በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 11 ነጥብ 8 ሚሊየን ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸው በጉራጌ ዞን የቸሀ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ነሐሴ 15/2014 ዓ.ም

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 11 ነጥብ 8 ሚሊየን ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸው በጉራጌ ዞን የቸሀ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የተተከሉ ችግኞች ከሰውና ከእንስሳት ንኪኪ በመከላከል እንዲጸድቁ አጽዕኖት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አመላክቷል የቸሀ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙንታቃ ናስር እንደገለጹት ማህበረሰቡ ቀድሞውን ችግኞችን የመንከባከብ ባህል ያለው በመሆኑ አሁንም ተግባራዊ እያደረገው እንደሆነ ተናግረዋል።

በዘንድሮው ለችግኝ የሚሆኑ ቦታዎችን ከመምረጥ ጀምሮ የጉድጓድ ዝግጅት ላይ ሰፊ ሰራ መከናወኑና ወቅቱን ጠብቆ እንዲተከል መደረጉን ገልጸዋል ።

በወረዳዉ በሁሉም አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 11 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞች መተከሉን አስረድተዉ ከዚህ ዉስጥም 35 ሺህ የሚሆኑት የፍራፍሬ ችግኝ መሆናቸውን አቶ ሙንታቃ ናስር አስታውቋል።

ችግኞቹ የተተከሉባቸው ቦታዎች የተጎዱና ለደን ልማት ምቹ በሆኑ ቦታዎች ላይ መሆኑም አመላክተዋል።

በዚህ አመት ከአምናው በተሻለ ሁኔታ የጽድቀት መጠን ከፍ ለማድረግ ከሰውና ከእንስሳት ንኪኪ እንዲርቁ የማጠርና አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚደረግ የገለጹት ኃላፊው ችግኞችን ከመትከል ባለፈ መንከባከቡ ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል ።

ደኖች ከተተከሉ በኃላ አስፈላጊውን እንክብካቤ የማድረግና እንዲጸድቁ ሁሉም ሰዉ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *