በዘንድሮው በተሰሩ የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች ከመንግስትና ከህዝብ ይወጣ የነበር 155 ሚሊየን 232 ሺ ብር ማዳን መቻሉን የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

በዞኑ የተጀመሩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን መምሪያው ገልጿል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ በዚህ ክረምት 1መቶ 41ቤቶች በአዲስ በመገንባትና በመጠገን ለአቅመ ደካሞች የማስተላለፍ ስራ ተሰርቷል። ይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሰራላቸው በማድረግ ተላልፏል ብለዋል።

በ16ቱ ዘርፎች 1መቶ 72ሺህ 6መቶ 32 ወጣቶች ተሳታፊ በሆኑበት በዘንድሮው የበጎ ተግባራት 4መቶ16ሺህ 2 መቶ33 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ኃላፊው ገልጸዋል።

አጠቃላይ በዘንድሮው በተሰሩ የበጎ ተግባራት በመንግስትና በህብረተሰቡ ይወጣ የነበረ 1መቶ 55 ሚሊየን 2መቶ 32ሺህ 3መቶ18 ብር ማዳን ተችሎአል ብለዋል፡፡

339 ሰንጋዎች ተገዝተው ለአረፋ በዓል ለአቅመ ደካሞችና የድሃ ድሃ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የቅርጫ ስጋ የማከፋፈል ስራ መሰራቱን የጠቆሙት ኃላፊው ለ36 ያህል የዘማች ቤተሰቦች በልዩነት ቤት እየተሰራላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም 19 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞች በበጎ አድራጎት ተግባር ለማከናወን ታቅዶ 23 ሚሊየን ጉድጓድ ተዘጋጅቶ ወጣቶች በመትከል ላይ መሆናቸው አስታውቀዋል።

በደም ልገሳ 8መቶ 81 ዩኒት ደም መለገሱንና በትምህርት መዝጊያ መጨረሻ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የሚሆን 6መቶ 22 ዩኒፎርም እና 5 ሺህ ደርዘን ደብተር መሰብሰቡ ጠቅሰዋል።

የወጣቱን ስብዕና ሊገነቡ የሚችሉ የወጣቶች ማእከላት እና የንባብ አገልግሎት የሚሰጡ ቤተመፃህፋት እድሳትና ግንባታ ላይ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው 3 መቶ 15 መፃህፍት በማሰባሰብ ለወጣት ማእከላት ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

የመንግስት ተቋማት፣ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ፣ባንክ ቤቶች፣ተራዶ ድርጅቶች፣ባለሀብቶች በማስተባበር ለ912 አቅመ ደካማና የድሃ ድሃ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት ለመገንባት ታቅዶ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ አመላክተዋል።

በወልቂጤ ከተማ የህዝብ ቤተመፃህፍት አየተገለገሉ ከገኘናቸው ወጣቶች መካከል ወጣት ሒክማ እና ወጣት ይድነቃቸው ፈቃዱ ይገኙበታል። ሁለቱም በሰጡት አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያ ተጥዶ ከመዋል ስብእናን ሊገነቡ የሚችሉ መፅሐፍትን ማንበብ የተሻለ መሆኑን አብራርተዋል።

በእውቀት እና በስነምግባር የታነፀ ወጣት ለሀገር እድገት ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎቹ የወጣቶች ማእከላት እና የንባብ ቦታዎች ምቹ የማድረግ ስራ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባና የወጣቱ ስብእና ግንባታ ላይ ቢሰራ ውጤታማ መሆኑ እንደሚቻል አስረድተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *