በዓላትን ምክንያት በማድረግ ከሚፈጠሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ ።

ጳጉሜ 3 /2014 ዓ/ም

በዓላትን ምክንያት በማድረግ ከሚፈጠሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ ።

ጅንአድ የተለያዩ ሸቀጦችን በጅምላ ዋጋ ለህብረተሰቡ ማቅረብ መጀመሩን ተጠቆመ።

በጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የሸማቾች ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ሲሳይ ይርሳልኝ እንደገለፁት የዞኑ ማህበረሰብ በዓልን ምክንያት በማድረግ ህገወጥ ነጋዴዎች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በፍጆታ እቃዎች ውስጥ ባእድ ነገር ስለሚያረጉ ህብረተሰቡ ከመሰል ችግሮች መጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በመንግስት በኩል የሚቀርቡ የፍጆታ እቃዎችን ወደ ዞኑ በማስገባት ለሁሉም ወረዳዎች በማከፋፈል ላይ መሆናቸውን ጠቁመው ከአሁን በፊት ከወልቂጤ ከተማው ወጥቶ የነበረውን ጅንአድ እንደገና ስራውን እንዲጀምር በማድረግ ቆርቆሮን ጨምሮ የተለያዩ ሸቀጦችን በጅምላ ዋጋ ለህብረተሰቡ ማቅረብ መጀመሩን አስረድተዋል።

በዞን ማእከል ላሉት የመንግስት ሰራተኞች ከክልሉ በተሰጠው ኮታ መሰረት በቡታጅራና በወልቂጤ ማእከል ዘይትና ስኳር ለማሰራጨት እና ዶሮና እንቁላል በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል ።

ሸማቹ ማህበረሰብም የገበያ አማራጮችን ሳያዩ ቸኩለው ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረግ አሳስበዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ችግሮች ካጋጠሙ በ8034 ነፃ የስልክ መስመር ህብረተሰቡ ጥቆማ ማድረግ እንደሚችል ገልጸዋል ።
መምሪያውም ግብረ_ሀይል በማዋቀር አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እየተሰራ ሲሆን ወጥ የሆነ የዋጋ ተመን እንዳይኖር የወቅቱ ዋጋ መዋዠቅ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ገልጸዋል ።

መምሪያው ባደረገው ምልከታም የዶሮ ዋጋ ከ6 መቶ እስከ 7 መቶ እንቁላል አሰከ 8 ብር ሽንኩርት ከ45 እስከ 50 ብር መሆኑን መገንዘብ ተችሏል።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *