በዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችንና የስነ ምግባር ችግሮችን በተገቢዉ በመቀረፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ።

መጋ

በስነ ምግባርና በቅን አገልጋይነት የተቃኘ ፐብሊክ ሰርቫንት ለለዉጡ ዘላቂነት በሚል መሪ ቃል ከሁሉም ወረዳዎችና ከወልቂጤ ከተማ አስተዳድር የተዉጣጡ የዉሃና ማዕድን ኢነርጂ ጽህፈት ቤቶች የስነ ምግባር ኦፊሰሮች በጸረ ሙስና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ እንዳሉት ሙስናና ብልሹ አሰራር ሀገር የሚያወድምና የሚያዳክም ከመሆኑም በተጨማሪ ማህበረሰቡ የሚፈልገዉን አገልግሎት በአግባቡ ለመስጠት ከፍተኛ እንቅፋት ይፈጠራል ብለዋል።

በመሆኑም ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመቀነስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2014 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነም አብራርተዉ በዞኑ አስተዳደር የስነ ምግባር ኦፊሰሮች ተመድበው ስራ መስራት ከጀመሩ ወዲህ ውጤታማ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

በዉሃና ኢነርጂ ጽህፈት ቤቶች የሚሰሩ ስራዎች ጠንቅቆ ማወቅ እንደሚገባም ተናግረዉ በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችንና የስነ ምግባር ችግሮችን በተገቢዉ መቀረፍ እንደሚገባም አመላከተዋል።

ከመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት አንጻር ትርፍ ክፍያዎች የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ ማስቆም የተቻለ እንደሆነም ጠቁመዉ በማዕድን ዘርፍ የሚስተዋለዉን ብልሹ አሰራር ለማስቀረት አጸኖት ተሰጥቶ የሚሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

ሴቶችና ወጣቶች በማዕድን ዘርፍ ተደራጅተዉ በመስራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም አስታዉቀዉ በዚሁ ዘርፍ ፍቃድ ወስደዉ የተደራጁ ማህበራት ከአባላቶቻቸዉ አንዱ ወይም ሁለቱ ብቻ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን ይህም መቅረት እንደለበትም ተናግረዋል።

አክለዉም ኃላፊዉ ተጋግዘን በመስራት በዘርፉ የሚለገዉን ዉጤት እንዲመጣ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ቅነጅታዊ አሰራሩን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አብራርተዋል።

ስልጠናዉን የሰጡት የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ ወ/ሮ ዳርምየለሽ አለሙ እንዳሉት በዉሃና መማዕድን ኢነርጂ ዘርፍ ሴቶችን ስለሙስና አስከፊነትና በሀገርና በህብረተሰቡ እያስከተለ ያለው ጉዳት በተገቢዉ በመረዳት የፀረ ሙስና ትግሉ መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።

ሰልጣኞችም በሰጡት አስተያየት ዉሃና መማዕድን ኢነርጂ ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ የሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ መምሪያው እያደረገ ያው ጥረት የሚበረታታና በቀጣይም ሰፋ ባለ መልኩ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አክለውም ስልጠናውን መነሻ በማድረግ ለባለሙያተኞች በሙስናና ብልሹ አሰራርና በስነ ምግባር ላይ ስልጠና ለመስጠትም እንዳለባቸዉም ማብራራታቸውን የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *