በወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲሁም በስፓርት ልማት ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

መጋቢ

በወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲሁም በስፓርት ልማት ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የ2016 የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን እንዳሉት ወጣቶች በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ በፖለቲካው ዘርፍ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል።

በስነምግባር የታነጹና በሀገር ልማት የበኩሉን አስተወጽኦ የሚያበረክቱ ወጣቶችን በመፍጠር እንዳለበትና ወጣቱ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በስፋት በማሳተፍ ጊዜያቸው፣ ጉልበትና ገንዘባቸው ለማህበረሰቡና ለሀገር እንዲያበረክቱ መስራት ይገባል ብለዋል።

ወጣቱና ማህበረሰቡ ጤናው በስፖርቱ ዘርፍ እንዲጠበቅ ማስ ስፖርት ላይ የተጀማመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አንስተዋል።

ተቋሙ ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት መሰራት እንዳለበት አቶ ፈይሰል ገልጸዋል።

በመምሪያው የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ አንሳ በበኩላቸው የወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም በዘርፉ በትኩረት መስራት እንዳለበት አስረድተዋል።

ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማሳተፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር በዘርፉ የተሻለ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።

የወጣቶች የስብዕና ማዕከላት በማጠናከርና ለታለመለት ዓላማ በማዋል ወጣቱ ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በመምሪያው የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር በዞኑ በስፖርቱ ዘርፍ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተተኪ ስፖርተኞችና አሰልጣኞችን ለማፍራት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸው ለዚህም ስልጠና እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በዞኑ የስፖርት አደረጃጀት፣ ታዳጊ ፕሮጀክትና የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት በማጠናከር ውጤታማ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።

ሀብት አሰባሰብ ላይ የሚመለከታቸው አካላት በማሳተፍ ከአርሶ አደር፣ ከነጋዴና ከመንግስት ሰራተኞች በተገቢው ሊሰበስቡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በግማሽ አመቱ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተከናወኑ ተግባራት 374ሺህ 210 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በዚህም ከመንግስትና ከህዝብ ይወጣ የነበረውን 203 ሚሊዮን 27ሺህ 1መቶ ብር ማዳን መቻሉንም ተናግረዋል።

በዞኑ ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች 8መቶ 89 ቤቶች በአዲስና በጥገና መገንባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በዞኑ በ16 መስኮች በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው ይህም በቀጣይ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት ሊሰራ ይገባል።

ወጣቱ በስነ-ምግባር የታነጸ ምክንያታዊ ወጣት ለማፍራት የወጣቶች የስብዕና ግንባታ ስራ ላይ ውስንነት መኖሩን ጠቅሰው ይህም በቀጣይ በበጀት በመደገፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት የስፖርት ማዘውተሪ ስፍራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው ይህም ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ስልጠና ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

ወጣቱ በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚና ተሳታፊ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *