በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የተጀማመሩ የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና የምርምር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ዩኒቨርስቲው አስታወቀ።


ዩኒቨርስቲው 5ተኛው አመታዊ ብሄራዊ የጥናትና የምርምር ኮንፈረንስ የሀገር ሽማግሌዎች፣በምርምርና ጥናት የተሰማሩ ተመራማሪዎች፣ሙህራኖችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሂዷል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉሪስ ደሊል እንደተናገሩት የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ በዩኒቨርስቲው በየ አመቱ የሚደረግ ሲሆን የዘንደሮውም”የሳይንስና የቴክኖሎጂ ቅንጅት ለአጠቃላይ እድገት”በሚል መሪ ቃል ኮንፈረንሱ እንዲካሄድ ተደርጓል።

በኮንፈረንሱም በሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣በተለያዩ ቦታዎች በምርምር ስራ የተሰማሩ ተመራማሪዎች፣የጥናትና የግኝት ውጤት ስራዎቻቸው የሚያቀርቡበት ሲሆን ዩኒቨርስቲውም የሚሰራቸው የምርምርና ጥናት እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራዎቹ ለሌሎች የሚያጋራበት ኮንፈረንስ መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ፋሪስ አክለውም ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ለጥናትና ምርምር ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑ የገለጹ ሲሆን ለአብነትም በእንሰት ምርት ላይ እንዲሁም በሀገር በቀል እውቀትና በሌሎችም የተጀማመሩ የምርምር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ተናግረዋል።

ዩኒቨርስቲው በቁና ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራትና ተመርቆ የሚወጣው ተማሪ በስነ ምግባር የታነጸ፣ስራ ጠባቂ ሳይሆን ስራ የሚፈጥር የሰው ሀይል ለማፍራት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል ዶክተር ፋሪስ።

የጅማ ዩኒቨርስቲ የስነ ምግብ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተፈራ በላቸው በኮንፈረንሱ ተገኝተው እንደተናገሩት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ እድገትና ምርታማነት ወሳኝ መሆኑ ባቀረቡት ጹሁፋቸው አመላክተዋል።

ሀያላን ሀገራት ለዚህ የደረሱት ሳይንስና ቴክኖሎጂ በአግባቡ በመጠቀማቸው ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ ኢትዩጵያ ይህንን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትቷን ለማረጋገጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራ መስራት ይጠበቅባታል ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም ወልቂጤ ዩኒቨርስቲም ዘርፉን በማጠናከር ለምርምርና ጥናት እንዲሁም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ስራው ለአካባቢውና ለሀገራችን እድገት ወሳኝነት እንዳለው አስታውቀዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የቦርድ አባል እና የባዮ ቴክኖሎጂ ተመራማሪ ዶክተር ካሳሁን ተስፋዬ በእለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በአለም የኢኮኖሚ እድገት ላይ ምን ድርሻ እንዳለውና የባዬ ቴክኖሎጂ ስራዎች በአሁን ወቅት በግብርና ዘርፍ ላይ እየፈጠሩት ያለ እድል በተመለከተ ጥናታዊ ጹሁፋቸው አቅርበዋል።

ሳይንስና ቴክኖሎጂን ተጠቅመን በግብርናው፣በጤናው፣በአየር ንብረት ለውጥ፣አጠቃላይ በኢንድስትሪው ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል የሚያሳዩ መሆናቸው አስገንዝበው ቀጣይ በዘርፉ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የምርምርና ጥናት ስራዎች ለማቅረብና ወደ ማህበረሰቡ ለማውረድ ግብአቶች የሚያሰፈልጉ በመሆናቸው በዩኒቨርስቲው የተጀማመሩ ስራዎች ዘርፉን የሚያነቃቁ በመሆናቸው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *