በወልቂጤ ከተማ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በአበሽጌ ወረዳ ማመዴ ቀበሌ በቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው በቅርቡ በተገነባው የረገ ኤያት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል ።

ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ እየተስተዋለ ያለውን የሙቀት መጨመር መግታት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ብረሃኑ በየነ በችግኝ ተከላው ወቅት እንደገለጹት እንድ ሀገር የተያዘው የአረንጌዴ ልማት አውን ለማድረግ “አሻራችን ለትውልዳችን “በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ለማሳካት ከዋናው መስሪያ ቤት ጀምሮ እስከ ቅርንጫ መስሪያ ቤት ድረስ ያሉ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች የችግኝ ተካላ እያከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሌሎች ተቋማት ዛፎችን በመትከል ማህበራዊ ግዴታውን ለመወጣት በአረንጓዴ ልማት በተለያዩ አከባቢዎች ችግኝ መትከላቸውን የገለጹት አቶ ብርሃኑ በቀጣይ የተተከሉት ችግኞችን በመንከባከብ የአየር ንብረት መዛባት እንዳይከሰት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉብርዬ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውዱ ወርቁ እንደተናገሩት ችግኞችን በተመረጡና በተጎዱ ቦታዎች በመትከል አርንጓዴና ዉብ ኢትዮጵያን ለመጪው ለትውልድ ለማስተላለፍ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኛች ከመደበኛ ስራቸው ጎን ለጎን በችግኝ ተከላው እየተሳተፊ ይገኛሉ ብለዋል ።

በችግኝ ተከላው ላይ ከተሳተፉት መካከል ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ ነስራላ መሀመድና የጆካ ቅርንጫ ባለሙያ ማርታ ሀ/ገብርኤል የተከሏቸውን ችግኞች በቀጣይ አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል ።

የማመዴ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ባህሩ ከድር እንደተናገሩት የመንግስት ተቋማት ሰራተኞችና ኃላፊዎች ችግኞችን ለመትከል በመምጣታቸው መደሰታችውን ገልጸው በእለቱ የተተከሉ ችግኞችን በአከባቢው ያሉት አርሶ አደሮች ተረክበው አስፈላጊውን እንክብካቤና ከከብት ንኪኪ እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።

በወልቂጤ ከተማ የሚገኙት 5 የባንኩ ቅርንጫፎች ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *