በወልቂጤ ከተማ የሚስተዋለው ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ 30 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ተጨማሪ ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች እንደሚቆፈሩ የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኤነርጂ መምሪያ አስታትወቀ።

የከተማው የውሃ ቦርድ በከተማው ውሃ ችግር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
የወልቂጤ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ የሚያገኘው ከሬቡ፣ ከቦዠባርና ከቃጥባሬ በተገነቡ ምንጮች ነው።
እነዚህ የውሃ ምንጮች የሚያመነጩት የውሃ መጠን በሰው ሰራሽና በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ነዋሪው በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሉ ቅሬታውን እየገለጸ ይገኛል።
የከተማው የውሃ መቆራረጥ ያሳሰባቸው የዞኑና የከተማው አስተዳደሮች የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ገብተዋል።
በየጊዜው የሚስተዋለው የንጹህ መጠጥ ውሃ መቆራረጥ ህብረተሰቡ ከሚያነሳቸው ችግሮች በዋናነት ይጠቀሳል።
የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኤነርጂ መምሪያ አቶ ፍስሃ ዳምጠው ይህን የውሃ ችግር ለመቅረፍ የዞኑ እና የከተማው አስተዳደሮች በጋራ 30 ሚሊዮን ብር በመመደብ ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ለማስቆፈር ከደቡብ ውሃ ስራዎች ድርጅት ጋር ውል የተገባ ሲሆን ግንባታው እስከ ሶስት ወራት ባሉ ጊዜያት ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የቦዠባር የውሃ ማመንጫ አካባቢ የሚስተዋለው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት መቅረፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከእምድብር ከተማ ደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል ጋር ውይይት ማድረግ የተቻለ ሲሆን የሀይል መቆራረጥ ችግር ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ አቅጣጫ እንደተቀመጠ ኃላፊው አብራርተዋል።
በከተማው የፋብሪካዎች፣ የሆቴሎችና የነዋሪዎች ቁጥር እያደገ በመሆኑ ከክልሉ ውሃ ማእድንና ኤነርጂ ቢሮ ጋር በመሆን ተጨማሪ ጥናቶች ተጠንተው ተጨማሪ ሀብት ለመፈለግ ይሰራል ብለዋል።
ሆኖም ግን በከተማው የሚስተዋለው የውሃ ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ በመሆኑ የውሃው ችግር እልባት እስከሚያገኝ ህብረተሰቡ በትዕግሥት ከመጠበቅ ባሻገር አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *