በወልቂጤ ከተማ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተገነባዉ ስራኖ ሆቴል ሰኞ መስከረም 16 የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት ለአገልግሎት (SOFT OPENING) በማድረግ ክፍት ይሆናል።

መስከረም 15/2015 ዓ.ም
በወልቂጤ ከተማ ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተገነባዉ ስራኖ ሆቴል ሰኞ መስከረም 16 የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት ለአገልግሎት (SOFT OPENING) በማድረግ ክፍት ይሆናል።

ደረጃዉን የጠበቅ ባለ 5 ፎቅ ሆቴል በወልቂጤ ከተማ የፊታችን ሰኞ ከጠዋቱ 2 ሰአት ጀምሮ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል።

በከተማዉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብቶች የበለጠ ተነሳሽነትን የሚፈጥረዉ የስራኖ ሆቴል ደረጃዉን የጠበቀ ግንባታ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ገንብቶ በማጠናቀቅ ሰኞ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።

በወልቂጤ ከተማ የወጣት ባለሀብት ዩሃንስና ሀይሌና ቤተሰቦች ትልቅ መሰረት የሆነዉን ባለ አምስት ፎቅ ግንባታ ለአካባቢዉ ማህበረሰብ፣ ለሌሎች እንግዶችና ቱሪስቶች ምቹና ጥራት ያለዉ አገልግሎት ይሰጣል።

በዚህ ዘመናዊ ሆቴል በዉስጡ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል ደረጃዉን የጠበቀ የመኝታ አገልግሎት ፣ ሁለት ባርና ሪስቱራንት ፣ የካፌ አገልግሎት ፣ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ የብሮድባንድ አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች ይሰጣል።

ሆቴሉ የፊታችን ሰኞ በክብር እንግዶች ሪቫን ተቆርጦ አገልግሎት የሚምር ሲሆን የሆቴሉ ዋና ምርቃት የሚደረግበትን ቀን በዉል አልታወቀምና በቀጣይ የምናሳዉቀ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *