በወልቂጤ ከተማ ከካምፕ እስከ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ድረስ ለሚገነባው የ3 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ስራ ተጀመረ!!

የከተማውን የውስጥ ለውስጥ መንገድ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አስታዉቋል!!

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዳለ ገብረመስቀል እንዳሉት በከተማው የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መሰረተ ልማት የማስፋት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህም በከተማው ከካምፕ ሰፈር እስከ ወልቂጤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ለሚገነባው የ3.2 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ስራ ከአበባው ሠለሞን ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር የውል ስምምነት መፈራረማቸውን ገልጸው በዛሬው እለትም የመንገድ ግንባታ ስራው መጀመሩን ጠቁመዋል።

በከተማው የተጀመሩ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ልማት ስራውም የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ከመመለሱም በተጨማሪ ለከተማዋ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው እንደሆነም አቶ እንዳለ ገልጸዋል።

በቀጣይም በከተማው የሚስተዋሉ የመንገድም ሆነ ሌሎች የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት ከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ተግቶ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ሔኖክ አብድልሰመድ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት ዘርፈ ብዙ ጠንካራ ጥረቶች እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በከተማው የተጀመሩ የልማት ስራዎች በታቀደለት ጊዜና በጥራት እንዲሰሩ ጠንካራ ድጋፍና የክትትል ስራዎች እንደሚደረጉም ገልጸዋል።

የመንገድ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከመንግሥት ባሻገር ህብረተሰቡ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም አቶ ሔኖክ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአበባው ሠለሞን ኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት አቶ አበባው ሠለሞን በበኩላቸው የመንገዱን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት ገንብቶ ለማስረከብ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

አቶ አበባው አክለውም ከካሳ ክፍያና ከሌሎችም የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ጋር ያሉ ችግሮች የማይጓተቱና የሚመለከተው አካል ክትትል የሚያደርግ ከሆነ ከውል ስምምነቱ ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩም መግለፃቸው ከከተማው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መረጃ ያመለክታል።

በመጨረሻም በከተማው ለሚሰሩ ለሶስት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ስራዎች ግብዓት ለማቅረብ የሚውለው የገረጋንቲ ማምረቻ [ኳሪሳይት] ቦታም በአመራሮች ተጎብኝቷል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *