በወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ የጉራጌ ዞን መምሪያ ሰራተኞች የተዘጋጁ ፕብሊክሰቪስ ባሶች ነገ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት መምሪያ ገለፀ።

ነሀሴ 11/2014 ዓ.ም

በወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ የጉራጌ ዞን መምሪያ ሰራተኞች የተዘጋጁ ፕብሊክሰቪስ ባሶች ነገ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት መምሪያ ገለፀ።

ለዚሁ አገልግሎት ከተዘጋጁ ሁለት ባሶች መካከል አንዱ ነገ በ12/12/14ዓ.ም አገልግሎት መሰጠት እንደሚጀር መምሪያው አስታውቋል ።

በዞኑ የመምሪያ ሰራተኞች የባስ አገልግሎትን ተጠቃሚ ለማድረግ የዞኑ ፕብሊክሰርቪስና የሰው ልማት መምሪያ ከዞኑ አስተዳደር ጋር ሰፊ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዙልፍ አለዊ ከባሱ ስምሪት አጀማመር፣ ከአገልግሎት አሰጣጥና ተያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ከየመምሪያው ከተውጣጡ ከሰው ሀብት ልማት ባለሞያዎች ጋር ተወያይተዋል ።

ወይዘሮ ዙልፍ አለዊ በውይቱ ወቅት እንደገለጹት የባስ ሰርቪስ አገልግሎት የሰራተኛው ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ ሰራተኛው በወቀቱ በስራ ገበታው ላይ በመገኘት ተገቢውን አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲሰጥ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል ።

በመሆኑም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ባለሞያዎች በተመደቡበት የስራ ዘርፍ ከሌላ ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ለጉራጌ ዞን መምሪያ ሲቪል ሰርቫንት አገልግሎት ለመስጠት ከተዘጋጁ ሁለት ባሶች መካከል አንዱ ነጌ በ12/12/2014 ዓ.ም አገልግሎት መሰጠት እንደሚጀር የገለጹት ሀላፊዋ ሁለተኛው ባስ በቅርቡ ስራ ለማስጀመር እየሠሩ መሆናቸውን ተናግሯል ።

የስምሪት አሰጣጡ አብዛኛው ባለሞያዎች ይገኙበታል በተባሉ አካባቢዎችና የመምሪያ ተቋማት ባሉበት አካባቢ መነሻ በማድረግ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

በባሶቹ አገልጎሎት አሰጣጥ ሂደት ወደ ተግባር ሲገባ ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በመከታተል ከባለድርሻ አካላት ጋር በውይይት ይፈታል ብለዋል ሀላፊዋ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት መምሪያው የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም በዘርፋ የሚነሱ የመልካም አስተዳር ችግሮችን በህግና መመሪያ መሠረት እንዲፈቱ ለማድረግ አያደረገው ያሉ ጥረቶች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ባሶቹ ስምሪት የሚሰጥባቸው ፌርማታዎችና መነሻና መድረሻ ሰዓት በተመለከተ እና ሌሎችም ዝርዝር አጠቃቀም የተመለከቱ ጉዳዮች በመምሪያው ቴሌግራም ቻናል ላይ ማግኘት እንደሚቻል ተገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *