በወልቂጤ ከተማ ለሚገኙ ዘማች ቤተሰቦች የአቢሲንያ ባንክ/የጆካ ቅርንጫፍ/ የመስቀል በአልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርቷል።

መስከረም 14/2015ዓ.ም

በወልቂጤ ከተማ ለሚገኙ ዘማች ቤተሰቦች የአቢሲንያ ባንክ/የጆካ ቅርንጫፍ/ የመስቀል በአልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርቷል።

የዘማች ቤተሰቦች በአልን ደስ ብሏቸዉ እንዲያሳልፉ ለተደረገላቸዉ ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

የአብሲንያ ባንክ የጆካ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ አሳየህኝ ያቆብ እንዳሉት ባንኩ ሁሌም ማህበረሰቡን ማገልገልና ከማህበሠሰቡ ጎን የሚቆም እንደሆነም ያስረዱት ስራ አስኪያጁ ለሀገር ብለዉ እየተዋደቁ ላሉ ለ50 የዘማች ቤተሰቦች ለሆኑ አባወራዎች 100 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ ሁለት በሬ በመግዛት ማዕድ ማጋራታቸዉም አስታዉቀዋል።

ባንኩ ቀደም ሲልም መማር እየቻሉ የትምህርት ቁሳቁስ ችግር ያለባቸዉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ ማድረጉም አስታዉሰዋል።

ማህበረሰቡን መደገፍና ማገዝ የባንኩ እሴት እንደሆነም አብራርተዉ ባንኩ ወደፊትም በዚህ አይነት በጎ ተግባርና ተያያዥ ጉዳዩች ላይ ከማህበረሰቡ ጎን እንደሚቆምም አመላክተዋል።

ከተባበርን በማህበረሰቡ ዘንድ የሚስተዋሉ ችግሮችን ማቃለል እንደሚቻል የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ሁሉም ሰዉ ከዘማች ቤተሰቦች ጎን በመሆን ድጋፍ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አብራርተዋል።

የባንኩ አጠቃላይ ሰራተኞችም ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ድጋፍ የሚያደርግ እንደሆነም ተናግረዉ ተቋማቶች አቅመ ደካሞችንና የዘማች ቤተሰቦችን ማገዝ እንዳለባቸዉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳድር ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ቃለአብ ደመቀ በበኩላቸዉ የመስቀል በአል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ በተለየ ሁኔታ የሚከበር በአል እንደሆነ ገልፀዋል።

የአብሲንያ ባንክ የዘንድሮ የመስቀል በአል ለዘማች ቤተሰቦች በሬ በመግዛት ድጋፍ ማድረጉም ተናገረዋል።

ባንኩ በክረምት ወቅት የተለያዩ ድጋፎች ማድረጉም አስታዉሰዉ ዘሬ ደግሞ የዘማች ቤተሰቦች በአልን በደስታ እንዲያሳልፉ ሁለት በሬ በመግዛት ማዕድ ማጋራቱም አሰረድተዋል።

የአብሲንያ ባንክ ለዘማች ቤተሰቦች ያደረገዉን ማዕድ የማጋራት ስራ ሌሎችም ተቋማት የራሳቸዉን አሰተዋጽኦ ማድረግ ይኖርባቸዋል በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

በማዕድ ማጋራቱ ላይ የተገኙ አንዳንድ የዘማች ቤተሰቦች በሰጡት አስተያየት በአሉ ደስ ብሎአቸዉ እንዲዉሉ የአብሲንያ ባንክ ያደገላቸዉ ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *