በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች ፎረም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በ12ኛ ክፍል ተማሪ የተሰራው ሮቦት ለእይታ ቀርቦ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።

በመንግስት በኩል ድጋፍ ከተደረገ በርካታ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ዕቅድ እንዳለውም ተማሪ ፍፁም ወርቁ ገልጿል።

ተማሪ ፍፁም ወርቁ የህዳሴ ፍሬ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰዎችን ተክቶ የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ ሮቦት መስራቱን ተናግሯል።

ሮቦቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ታግዘው የተሰራ መሆኑን የገለፀው ተማሪው በተለያዩ ቋንቋዎች ትዕዛዞችን እየተቀበላ የሚያስተናግድ መሆኑንም ተናግሯል።

በእንቅስቃሴ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አልፎ አገልግሎት የሚሰጥ ስለመሆኑም ገልጿል።

ሮቦቱ እየተንቀሳቀሰ አገልግሎት ከመስጠቱም በተጨማሪ መንቀሳቀስ የማይችሉ አካል ጉዳተኞች አፕልኬሽን በመጠቀም ትዕዛዝ ሲሰጡ የሚቀበል እንደሆነም ተማሪው አስረድቷል።

ወጣቱ ከዚህ በተጨማሪም ለጤናና ግብርና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት ዕቅድ እንዳለው ተናግሯል።

በቅርቡ በድሬዳዋ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የፈጠራ ስራዎች ውድድር እንደሚሳተፍም ገልጿል ።

የወጣቱን የፈጠራ ስራ የጎበኙ አንዳንድ ግለሰቦች በበኩላቸው ባዩት ነገር እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው መንግስት እንደዚህ አይነት የፈጠራ ስራ የሚሰሩትን ሊያበረታታ ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አምዱ ካሚል እንዳሉት እንደ ከተማው በፈጠራ ስራዎች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን መንግሰት እንደሚደግፍ አስረድተዋል ።

ተማሪ ፍፁም ወርቁ የጀመራቸው የፈጠራ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋ ሲል የዘገበው የወልቂጤ ከተማ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው።
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *