በክረምት የበጎ አድራጎት ስራ ለ35 ሺህ 250 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

ነሐሴ 16/2014

በክረምት የበጎ አድራጎት ስራ ለ35 ሺህ 250 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

በ16ቱ የበጎ አድራጎት ተግባራት ማህበረሰባቸው እያገለገሉ እንደሆነ በወረዳው በበጎ አድራጎት ተግባር የተሰማሩ ወጣቶች ተናገሩ።

የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ይታያል ምህረት በወረዳው ከ12 ሺ በላይ ወጣቶች በማሳተፍ በ16 ዘርፎች የበጎ አድራጎት ስራቸው እያከናወኑ ይገኛሉ።

በክረምት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር 1ሚሊየን 2መቶ 40 ችግኞች በበጎ አድራጎት ስራ የተተከሉ ሲሆን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች 27 ተማሪዎች የማጠናከርያ ትምህርትና የኮምፒውተር ስልጠና እየሰጡ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዚህ የክረምት በጎ ተግባር 20 ድልድዮች በአዲስና በጥገና መልኩ መሰራታቸው የተናገሩት ኃላፊው አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች 10 ሄክታር መሬት ታርሳል።

እንደ ይታያል ገለጻ በበጎ አድራጎት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሰሩት አንዱ የቤት ጥገና ሲሆን ባለሀብቱ፣ ነጋዴውና ማህበረሰቡ በማስተባበር እስካሁንም 5 ቤቶች መሰራታቸው ተናግሯል።

በከተማና በገጠር ከሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እስከ 27 ሺህ ብር የሚሆን ገንዘብ በማሰባሰብ በባዓላት ወቅት አቅም ለሌላቸው ወገኖች ማእድ የማጋራት ስራ ተከናውኗል ብለዋል።

ከወረዳው መንግስት ጋር በመተባበር ለ1 የዘማች ቤተሰብ ቤት መሰራቱን በመጠቆም።

የበጎ አድራጎት ስራ ከተጀመረ ቀን አንስቶ በተሰሩ ስራዎች ለ35ሺህ 250 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ኃላፊው ተናግሯል።

በዚህ የበጎ አድራጎት ተግባር ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ሊወጣ የሚችለው ከ5ሚሊየን 6መቶ ሺ ብር በላይ ማዳን እንደተቻለ አብራርተዋል።

ዶ/ር ኤሊያስ አደገና ወጣት መሀመድ ኑር በወረዳው የበበጎ አድራጎት ስራ የተሰማሩ ሲሆኑ በአካባቢ ጽዳትና ውበት፣እርሻ በማረስ ፣ለአረጋውያን ቤት በመስራት፣ትምህርት በማስተማርና በሌሎች በ16ቱ ዘርፎች ለማህበረሰባቸው አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ገልጸዋል።

ወ/ሮ መዲና አህመድ በወረዳው ቤት የተሰራላቸው እናት ሲሆኑ ከዚህ በፊት ቤታቸው ደሳሳ በመሆኑ የተነሳ በዝናብና በውርጭ ይደርስባቸው የነበረ እንግልት እጅግ አሰቃቂ እንደነበር ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *