በክረምት ወራት በወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገኙ ውጤቶች በበጋው ወራትም መድገም እንደሚያስፈልግ የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ጥቅምት 3/2015 ዓ/ም

በክረምት ወራት በወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገኙ ውጤቶች በበጋው ወራትም መድገም እንደሚያስፈልግ የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ወጣቶች የህብረተሰቡ የመቻቻል፣ተደጋግፍ የመኖርና ችግሮቹ በጋራ የመፍታት እሴት ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለጸ።

የ2014 ዓ.ም የወጣቶች የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና የ2015 ዓ.ም የበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ በቆሼ ከተማ ተካሂዷል።

የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ብላቱ እንዳሉት በጉራጌ ዞን በወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት እየተሰራ ያለው ስራ በክልሉ ግንባር ቀደም ከሆኑ አካባቢዎች ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

በክረምት ወራት የታዩ የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት በበጋው ወራትም መድገም እንደሚያስፈልግ አቶ ተስፋዬ ብላቱ ተናግሯል።

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመንግስት በጀትና በአንድ ተቋም ብቻ የሚሸፈን ባለመሆኑ ተቋማትም እንደተቋማቸው የስራ አይነት አያይዘው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት የዞናችን ህዝብ በአብሮነትና በመቻቻል የኖረ ህዝብ በመሆኑ ወጣቶች የህብረተሰቡ የመቻቻል፣ተደጋግፍ የመኖርና ችግሮቹ በጋራ የመፍታት እሴት ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው የዘንድሮ ስራም አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዞኑ ለተቸገሩ ወጎኖች ልዩ ትኩረት በመስጠት ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የማጤመ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን ከ1 ነጥብ ሚሊየን በላይ ብር የውልቸር ድጋፍ መደረጉ አስገንዝበዋል።

የበጎ አድራጎት ተግባሩ በበጋውም ውጤታማ ለማድረግ ከወጣቶች፣ ከሀይማኖት ተቋማት፣ከተራዶ ድርጅቶች ከባለሀብቱና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

እንደ አቶ መሀመድ ገለጻ በዞኑ በተሰሩ ስራዎች በተለያዩ ዘርፎች ውጤት የታየበት ሲሆን ለአብነትም በትምህርት፣ በጤና በግብርና በማህበረሰብ ልማት፣በሰላም እሴት ግንባታና በተለያዩ ዘርፍ የሚሰራው የበጎ አድራጎት ተግባር በማህበረሰቡ እድገትናና ለውጥ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው አስታውቋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጅማቶ እንደገለፁት በዞኑ በጎነት በህዝባችን ውስጥ ባህል ሆኖ የኖረ ቢሆንም አቅመ ድካማ ለሆኑ ወገኖች አረጋዊያን የአእምሮ ህሙማን በተለያዩ ክስተቶች ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችና በሌሎችም በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ ተደርጓል።

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 8 መቶ 7 ቤቶች በአዲስና በጥገና መልክ የተሰራ ሲሆን 4ሺ 8መቶ ቤተሰቦች ተጠቃሚ መሆናቸው አቶ አወል አብራርተዋል።

በ16ቱ ዘርፎች 2መቶ 70 ሺ ወጣቶች በማሳተፍ 8መቶ 40ሺ 6መቶ 2 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የተናገሩት አቶ አወል ከህዝብና ከመንግስት ይወጣ የነበረው 2መቶ 37 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ማዳን መቻሉ አመላክቷል።

የመምሪያው ምክትልና የወጣት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ በ2015 ዓ.ም በበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 1መቶ 98ሺ340 ወጣቶች በማሳተፍ 538 ሺ52 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል።

አክለውም 1መቶ 81 ሚሊየን 1መቶ 42ሺ 649 ብር ከመንግሥትና ከህብረተሰቡ የሚወጣ ገንዘብ ለማስቀረት መታቀዱ አስገንዝበው 1ሺ 8መቶ 18 ዩኒት ደም ይሰበሰባል ሲሉ አብራርተዋል።

በመድረኩ የተሳተፈ አካላት እንዳሉት በየ መዋቅሩ በተሰሩ የበጎ ስራዎች የተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወት መቀየር ቢቻልም ቀጣይ ግን በርካታ ስራዎችን አጠናክሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ስራው ውጤታማ እንዲሆን ሲያደርጉ የነበሩ ወጣቶች፣መምሪያዎች፣ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተሸለሙ ሲሆን ከወረዳ መዋቅር 1ኛ,እኖር ወረዳ 2ኛ,ቸሀ ወረዳ 3ኛ,ማረቆ ወረዳ ሲሆኑ ከመምሪያ 1ኛ ጤና መምሪያ 2ኛ,ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ 3ኛ,ትምህርት መምሪያ የዋጫ ተሸላሚ ሆነዋል። በተጨማሪም ከከተማ አስተዳደሮች በተሻለ አፈፃፀም ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋንጫ መሸለም ችሏል።

በእለቱም በቆሼ ከተማ የሚኖሩ የአንድ አቅመ ደካማ እናት ቤት በአዲስ ለመገንባት ቤቱን በማፍረስ የበጋ ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ በይፋ ተጀምሯል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *