በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።

ጷጉሜ 04/2014

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 21 ሺህ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሆኑም ተገልጿል ።

የእምድብር ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፈ ዱላ እንደተናገሩት የክርምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት 2 ቤቶች አዲስ አፍርሶ ግንባታና 6 ቤቶች እድሳት፣ 49 ዩኒት ደም ልገሳ ፣ የወጣት ማዕከላትን ማጠናከር፣ 1 ሺህ 6 መቶ የተለያዩ መጻህፍቶች ለወጣት ማዕከላት የማሰባሰብ ስራ፣ ከዚህ በፊት የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብና ሌሎችም ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ዘረፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።

በከተማው 9 መቶ 86 ሺህ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞች መተከሉን የገለጹት አቶ ሰይፈ ዱላ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 8 ሺህ 7 መቶ በላይ ወጣቶች በማሳተፍ 21 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ከማህበረሰቡና ከመንግስት ሊወጣ የነበረን 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ገንዘብ ማዳን መቻሉን ጠቁመዋል ።

ወጣቶች ማህበረሰባቸውን በማገልገል የጀመሩትን በጎ ተግባር በማጠናከር በገንዘብ የማይተመን የህሊና እርካታ ማግኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

እምድብር ከተማ ገበያ ሰፈር ቤት ከታደሰላቸው አረጋዉያን መካከል ወይዘሮ ኑሬያት ጃቢር እንደገለጹት ከዚህ በፊት የሚኖሩበት ቤት እንደሚያፈስና ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው እንደነበር ተናግረዋል ።

አሁን በክረምት የወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው በመታደሱ መደሰታቸውንና ችግራቸው እንደተቀረፈላቸው ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *