በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የቸሀ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ገለጸ

ነሐሴ 17/2014
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን የቸሀ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ገለጸ።

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ25 ሺህ 3 መቶ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሆኑም ተገልጿል ።

የቸሀ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ኑረዲን እንዳሉት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት 45 ቤቶች አዲስ አፍርሶ ግንባታና 38 ቤቶች እድሳት፣ 1 መቶ 75 ሄክታር የዘማች ቤተሰብና አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ከፍሎች የእርሻ አገልግሎት ፣ የደም ልግሳ፣ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ፣ወኃ ያቆሩ ዲቾች እንዲያፋስሱ የማድረግ ና ሌሎች ስራዎች ማከናወናቸውን ተናግረዋል ።
በወረዳው በሁሉም አካባቢዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች እንደተተከሉ የተናገሩት አቶ ተስፋዬ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱም 13 ሺህ 2 መቶ 7 ወጣቶችን በማሳተፍ እስካሁን 25 ሺህ 3 መቶ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሆኑም ገልጸዋል ።

በዚህም ከመንግሥትና ከማህበረሰቡ ሊወጣ የነበረ 15 ሚሊየን 6 መቶ 52 ብር በላይ ማዳን መቻሉን አቶ ተስፋዬ ኑረዲን አመላክተዋል ።

ወጣቶች የጀመሩትን በጎ ተግባር በማጠናከር ማህበረሰባቸውን በመጥቀም በገንዘብ የማይተመን የህሊና እርካታ ማገኘት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ወርበጬና ወሸርቤ ቀበሌ ቤት ከተሰራላቸው አረጋዉያን መካከል ወይዘሮ ሺመናት ሀድራ እንደገለጹት ከዚህ በፊት የሚኖሩበት ቤት እንደሚያፈስና ሊወድቅባቸዉ ደርሶ እንደነበር ተናግረዋል።

አሁን በክረምት የወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው በአዲስ በመሰራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *