በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ 35 ሚሊዮን ችግኞች በሴቶች ለመትከል ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ከጉራጌ ዞን፣ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የሊግ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የፓርቲው አባላቶች በእዣ ወረዳ በኔሸ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄዱ።

የጉራጌ ዞን የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ሀይሉ በዘንድሮ የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ ተግባር እውን ለማድረግ በሴቶች ብቻ 35 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ከተጣለው ግብ እስካአሁን 1ሚሊዮን 665 ሺህ በላይ ችግኞች ተተክለዋል ተብለዋል።

አንድ ሴት 1መቶ ችግኝ እንድተክል የሚል ሀሳብ በመያዝ ሴቶች በጓሮዋቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው በተለይ የቅመማ ቅመም፣የፍራፍሬና የውበት ችግኞች በመትከል ላይ መሆናቸው ተናግሯል።

የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ቦታው የመከለልና የኩትኳቶ ስራ እንደሚሰራ ያስታወቁት ወ/ሮ ዝናሽ 8ሺ 8መቶ ሄክታር መሬት በችግኝ ተከላው ይሸፈናል ብለዋል።

በዚህ ክረምት እንደ ቀድሞ ጊዜ ሴቶች በሀገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ያሉት ኃላፊዋ በተለይም በበጎ አድራጎት ስራ፣በቦንድ ግዢ፣በቁጠባና በግብርና ስራው በንቃት እንደሚሳተፋ ገልጸዋል።

ሴቶች መሰል አይነት ፕሮግራሞች ሲያከናውኑ በተለይም ችግኝ ሲተክሉ የችግኝ ጥቅም እንዲያውቁና የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉበት እድል ይፈጥርላቸዋል ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ፈቀደ እንደተናገሩት” ኢትዮጵያ በደን ትሸፈናለች” በሚል መሪ ቃል በወረዳው የሴቶች አደረጃጀት በማጠናከር ሴቶች ሀገራዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ ይገኛሉ።

ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎን እንዲህ አይነት ስራዎች መከናወናቸው ሴቶች የፖለቲካ አቅማቸው፣የመስራት ክህሎታቸውና እኩልነታቸው ከማሳየቱ በተጨማሪ የእርስ በርስ ትውውቅ እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሙንተሀ ሽሁር፣ወ/ሮ ሲቲ በሽርና ወ/ሮ ሽታዬ ሀሰን ችግኝ ሲተክሉ ያገኘናቸው ሴቶች ሲሆኑ ለቀጣይ ትውልድ ምቹ አካባቢን ለማስረከብ የችግኝ ተከላ ስራው ወሳኝነት አለው ብለዋል።

ከዚህ በፊት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ልምድ እንዳላቸው ያስታወሱት ሴቶቹ ቀጣይም ችግኞች መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞች እንደሚንከባኩም አስታውቀዋል።

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ገለጻ የመሬት መራቆትን የሚከላከሉ ችግኞችን ከመትከል በተጨማሪ የኑሮ ውድነቱን የሚያረጋጉና ለምግብነት የሚዉሉ ፍራፍሬዎች እንዲሁም የጓሮ አትክልቶችን በስፋት እንደሚተክሉ ተናግረዋል።

በእለቱም አጠቃላይ የዞኑና የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ሴቶች ሊግ የስራ አፈጻጸም በመገምገም ፕሮግራሙ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *