በክልል የክለቦች ሻምፕዮና ጉራጌ ዞን ወክሎ እየተሳተፈ የሚገኘው የቡኢ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።

የቡኢ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የ2015 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የስፖርት ሻምፒዮና በ3ኛነት ደረጃ አጠናቅቆ የደቡብ ክልል ባዘጋጀው ውድድር ተሳታፊ መሆን ችሏል።

በመሆኑም ግንቦት 21/2015 በ9:00 ቡኢ ከተማ ከብሩህ ተስፋ ቡድን በተደረገው ውድድር ቡኢ 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

የቡኢ ከተማ እግር ኳስ ቡድን በዚህ ጨዋታ በክልሉ የክለቦች ውድድር 4 ውስጥ መግባቱንና በቀጣይ ወር ሰኔ 3/2015 ላይ በሚደረገው የመላው ሀገር አቀፍ የክለቦች ጨዋታ ላይም እንደሚሳተፍ ታውቋል።

መላው የስፖርት አፍቃሪያን እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *