በክልሉ የሚገኙ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ሌሎችም ባህላዊ እሴቶችን ለማልማትና ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ከጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር 4ኛው ክልል አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ በቡታጅራ ከተማ አካሂዷል።

በጉባኤው በደቡብ ክልል የሚገኙ በተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችንና ህዝቦች ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተዘጋጁ 10 መጽሀፎች ተመርቀዋል።

የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትልና የባህል ቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አቡቶ አኒቶ በምረቃ ስነ ስርአቱ ተገኝተው እንዳሉት በክልል የሚገኙ የብሔር ብሔረሰቦችን ታሪክ፣ ቋንቋና ታሪክ ለማልማትና ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል።

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በርካታ የራሳቸው የሆነ ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ያላቸው በመሆኑ እነዚህን የማህበረሰቡን ማንነት የሚገልጹ ቋንቋ፣ ታሪክና ባህላዊ እሴቶቻቸውን በአግባቡ ተሰንድው ከማስቀመጥ አንጻር ውስንነት መኖሩ ገልጸው ይንንም ችግር ለመቅረፍ ቢሮው ከሙህራንና ከዩንቨርስቲዎች ጋር በመሆን እየሰራ ይገኛል።

የጥናትና ምርምሩ መካሄድ የህብረተሰቡን ቱባ ባህላዊ እሴቶች ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፉ እንዲዋወቁ ከማድረጉ ባለፈ ለቀጣይ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ጸሀፍት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አንዳለውም ገልጸዋል።

ቢሮው የብሔር ብሔረሰቦችን ባህላልና ታሪክ ሰንዶ በማስቀመጥ ለትውልድ እንዲተላለፍ እየሰራ ቢሆንም በቂ አይደለም ያሉት ኃላፊው በርካታ ቱባ እሴቶችን ከመኖራቸው የተነሳ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በቀጣይም ብሔረሰቦች የራሳቸውን ባህል እንዲያሳድጉ ከሚደረገው ስራ ጎን ለጎን የጋራ እሴቶችን የበለጠ በማሳደግ የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጠናከር የሚመለከታቸው አካላት በዘርፉ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው ቢሮው ከዩንቨርስቲዎችና ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን የደቡብ ክልል ብሔር ብሔረሰቦችን ታሪክ፣ ቋንቋና ባህል አስጠንቶ ለምረቃ በማብቃቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጥናትና ምርምር በማካሄድ በመጽሀፍት መልኩ በመሰነዳቸው ትውልዱ ቱባ ባህላዊ እሴቶችን እንዲያውቅ ከማድረግ በተጨማሪ ለትውልድ ለማስተላለፍ አስተዋጽኦው ከፍተኛ እንደሆነ ወይዘሮ መሰረት አስረድተዋል ።

በቀጣይ ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመቀናጀት የጉራጌ ብሔር ብሔረሰቦችን ታሪክ፣ ቋንቋና ባህላዊ እሴቶችን ለማሳደግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

አቶ ታደሰ ለገሰ የጉራጌ የስራና ቁጠባ ባህል እና አቶ መለሰ አብዴ የሀዲያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ የሚሉ ጥናቶችን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የማህበረሰቡን ቱባ ባህላዊ እሴቶችን በማጥናት በመጽሀፍ መልኩ መሰነድ ትውልዱ ባህሉን፣ ቋንቋውና ታሪኩን በሚገባ እንዲያውቅ ከማድረግ ባለፈ ከመጥፋት ለመታደግ ያግዛል።

የክልሉ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በርካታ ቱባ ባህላዊ እሴቶች ቢኖራቸውም እነዚህን አጥንቶ ከመሰነድ አንጻር ውስንነት መኖሩን ጠቁመው በቀጣይ ምሁራን፣ ዩንቨርሲቲዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸው ሊወጡ እንደሚገባ አመላክተዋል።

በቀጣይም መሰል ስራዎችን በማጠናከር የማህበረሰቡን እሴቶችን አጉልቶ ለማውጣት እንደሚሰሩም አመላክተዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት የጥናትና ምርምሩ መካሄድ የብሔር ብሔረሰቦችን ባህል፣ ቋንቋና ታሪክና ሌሎችም እሴቶችን ከመጥፋት ከመታደግ ባለፈ እሴቶቹን በሌሎች ብሔረሰቦች እንዲተዋወቁ ያደርጋል።

በቀጣይም ፣ ከዩንቨርሲቲዎችና ምሁራን ጋር በመሆን መሰል ስራዎችን በማጠናከር የማህበረሰቡን እሴቶችን አጉልቶ ማውጣት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም መጽሀፍቶቹ ለምረቃ እንዲበቁ ላደረጉ አካላት የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *