በኩርባ መንገድ ላይ መኪና እንዳይጋጭ ቴክኖሎጂ የፈጠረዉ ስለ ተማሪ ዳንኤል መንግስቱ በጥቂቱ።

መበኩርባ መንገድ መኪና እንዳይጋጭ ከርቀት እያሽከረከሩ ጥቆማ የሚሰጥ ቴክኖሎጂ በጉራጌ ዞን አገና ከተማ የ11ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ መፍጠሩን ጠቁሟል።

በሀገሪቱ በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሰዉ ህይወት መጥፋትና የንብረት ዉድመት መከሰት መስማት የዘወትር ዜና በሆነበት ሁኔታ በተማሪ ዳንኤል መንግስቱ የተሰራው ቴክኖሎጂ አደጋ ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ ነዉ።

ጉራጌ ዞን እንደ ኢዘዲን ካሚል አይነት በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ተማሪዎች በፈጠራ ስራ ላይ የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉ ቴክኖሎጂ ለመፍጠር ሲተጉና ሲለፉ ይስተዋላል።

ተማሪ ዳንኤል መኪኖች ኩርባ ባሉባቸዉ አካባቢዎች ላይ ተጋጭተው አደጋ እንዳያደርሱ እያሽከረከሩ ከፊት ለፊት መኪና እየመጠ እንደሆነ ጥቆማ የሚሰጣቸዉ አዲስ ቴክኖሎጂ ነው።

በትምህርት ቤቶች ላይ የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች በተማሪዎችና በመምህራን እየተሰሩ እንደሆነም ይታወቃል ሆኖም በዘርፉ የማህበረሰቡ ቁልፍ ችግር የሆኑ ቴክኖሎጂዎች መፍጠርና ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲዉሉ ማድረግ ይገባል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *