በከተሞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለቸው ችግኞችን በመትከል አርንጓዴ እንዲሆኑና ምቹ የአየር ንብርት እንዲኖራቸው ሴቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተገለጸ።

ግን

የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አሻራዬን አኖራለሁ በሚል ከተማዊ የችግኝ ተከላ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ዙልፋ አለዊ በወቅቱ እንደገለጹት ከተሞች አረንጓዴ እንዲሆኑና የተመቻቸ የአየር ንብረት እንዲኖራቸው ሴቶች የበኩላቸውን ሚና መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ምግቤን ከጓሮዬ በሚል የተጀመሩ የከተማ ግብርና ስራዎች በማጠናከር ሴቶች በኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል ።
ችግኞች ከተተከሉ ቡኃላ እንዳይደረቁ የመንከባከቡ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወይዘሮ ዙልፋ አለዊ አሳስበዋል ።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ዝናሽ ሀይሌ እንደተናገሩት ሴቶች በከተሞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለቸው ችግኞችን በመትከል አርንጓዴ እንዲሆኑና ምቹ የአየር ንብርት እንዲኖራቸው የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አስታውቀዋል።
ከዚህ በፊት የተተከሉ ችግኞች ከመትከል ባለፈ ለአገልግሎት እንዲበቁ እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊዋ ተናግረዋል ።

የወልቂጤ ከተማ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ስንታየሁ ሀሰን እንደተናገሩት ከተሞችን ውብ ለማድረግ በቀጣይ በተመረጡ ቦታዎች የችግኝ ተከላ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በእለቱም ካነጋገርናቸው መካከል ወይዘሮ ላምሮት አረጋኸኝ እና ሲሚራ ከድር እንደገለጹት አሁን ወቅቱ ለአረንጓዴ አሻራ ለችግኝ ተካላ ምቹ ወቅት በመሆኑ በየግቢያቸው እንደሚተክሉና የተከሉዋቸውም ችግኞች እንደሚንከባከቡ ተናግረዋል።

በዝግጅቱም የዞንና የከተማ ሴት አመራሮች ፣የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች እና ሴት የመንግስት ሰራተኞች ሊግ ማህበር ፊድሬሽን አደረጃጀትና የቀበሌ የልማት ቡድንች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *