በከተሞች ከይዞታ ማረጋገጫ ተያይዞ የተነሱ ችግሮች ለመፍታት በባለፈው 1 ወር ብቻ ለ1ሺህ 50 አርሶአደሮች ሚስጥራዊ ኮድ ያለዉ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ሰነድ መስጠት መቻሉም የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ገለፀ።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በቅርብ በከተሞች ከህዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ሰፊ ጥያቄዎች መነሳታቸው በማስታወስ በታቀደው የ90 እቅድ መሰረት ባለፈው 1 ወር ችግሮቹ ለመፍታት ምን ተከናውነዋል በሚል የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ታምራት ውድማ ጠይቆዋል።

መምሪያው ህዝብ በየደረጃው ያነሳቸዉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት የ90 እቅድ ታቅዶ በየደረጃው ከሚገኘው መዋቅር፣ከመምሪያው ማነጅመንትና ሰራተኞች ጋር መግባባት በመፍጠር ወደ ተግባር መገባቱ ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት ዉድማ የ90 እቅድ አፈፃፀማቸው በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ ከህገወጥ መሬት ወረራ ጋር ተያይዞ እስካሁን ባለዉ የቅድመ መከላከል ስራ በመስራት ረገድ 509 ይዞታዎች ላይ መስራታቸዉና 1ሺህ 2 መቶ 27 ግንባታዎችን የማፍረስ ስራ መከናወኑንና 1 መቶ 84 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ማድረግ ተችሏል።

ከመሬት ሀብት ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሁለት ወራት ዉስጥ በቅርበት በመከታተልና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለዉ የይዞታ ፋይል አደረጃጀት በተለይ የመሬት አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣ ሰዉ የሚንገላታበት ሁኔታ መኖሩምና በምሬት ጥያቄዎች መነሳቱ አስታዉቀዉ በአንድ ወር ዉስጥ 2 ሺህ 50 የይዞታ ፋይል የማደራጀት ስራም መሰራቱም አስረድተዋል።

አክለውም ሀላፊው በዞኑ በጊዜ ገደብ ያለሙ ቦታዎች ላይ ሰፊ ቅሬታ መኖሩ ገልፀው በከተማ ደረጃ በዚህ 262 ለኢንቨስትመንት የተላለፉ ይዞታዎችን የለዩበት ሁኔታ መኖሩም አብራርተዉ በዚህም 63 የይዞታ ቦታዎች ላይ እርምጃ መዉሰዳቸዉና 73 ሺህ 652 ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ የማድረግ ስራም ማከናወናቸዉምና በዚህ አንድ ወር ዉስጥ ብቻ 5 ሺህ 27 ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ አንዲገባ ማድረጋቸዉም አመላክተዋል።

ህገወጥነት ከመከላከል ጋር በተያያዘ ማስፋፊያ አካባቢዎች ላይ ያሉ አርሶአደሮች ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ሰነድ የመስጠት ስራ የተሰራ ሲሆን በበጀት አመቱ ለ1ሺህ 50 አርሶአደሮች ሚስጥራዊ ኮድ ያለዉ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ደረጃዉን የጠበቀ ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ሰነድ መስጠት መቻላቸዉም አስረድተዋል።

በዚህ አንድ ወር ዉስጥ 107 ማስፋፊያ አካባቢዎች ላሉ አርሶአደሮች ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ሰነድ መስጠት እንደቻሉም አቶ ታምራት ተናግረዋል።

በህገወጥ መንገድ የአጠና ንግድ ስራ ላይ መንገዶች ዘግተዉ የሚሰሩ 16 ግለሰቦች በማንሳት እና ተለዋጭ ቦታ ተመቻችቶላቸዉ እንዲሰሩ መደረጉም አስረድተዋል።

በስፋት የመሬት ወረራ የተከናወነባቸዉ አካባቢዎች መኖራቸዉም አስረድተዉ ለአብነት ወልቂጤ ከተማ በማንሳት ወረራዉን ለመከላከል የጀመሩት ስራ መኖሩም አመላክተዉ ህገወጥ ቤት ፈረሳ ባከናወኑበት ማግስት ድጋሚ የመዉረር ነገር የሚስተዋል እንደሆነና ቡታጅራ ከተማ አካባቢም በህገወጥ ወረራ ተመሳሳይ ድርጊት መኖሩንና ይህንንም በዘላቂነት ለመቅረፍ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽዕኖት ሰጥተዉ እየሰሩም እንደሆነም ገልጸዋል።

በዞኑ ዉስጥ በአዲስ የፈርጅ ለዉጥ ያደረጉ የአገና ከተማ ፣ የአርቅጥ ከተማና ኢንሴኖ ከተማ አስተዳደሮች በተሟላ መንገድ ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች ለማከናወን በ90 ቀን እቅዳቸዉ ዉስጥ መያዛቸዉ እነዚህ መዋቀሮች አካባቢ መሬት ላይ የሚወርዱ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያከናዉኑ ልዩ ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነም አስታዉቀዉ በነዚህም አካባቢዎች የመብራት ዝርጋታ፣ የገረጋንቲ ንጣፍና ሌሎችም ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑም አብራርተዋል።

የማህበራት ቤት መስሪያ ቦታ ጋር ተያይዞ በርካታ ማህበራት ተደራጅተዉ ቦታ ያላገኙና ቅሬታ ያለበት ሁኔታ መኖሩም አስታዉቀዉ በዞኑ ከ2 መቶ በላይ ማህበራት ተደራጅተዉ ቤት መስሪያ ቦታ እየጠበቁ እንደሆነም አስታዉሰዋል።

በዚህ በጀት አመት ዉስጥ ለ90 ማህበራት መሬት በማዘጋጀት ማስረከብ መቻሉ አስታዉቀዉ በዚህ አንድ ወር ዉስጥ ለ13 ለተደረጁ ማህበራት የቦታ ትልልፍ ማድረጋቸዉም አስታዉሰዋል።

በቀጣይ ተደራጅተዉ መሬት ላልተላለፈላቸዉ ማህበራት መሬት ለማስተላለፍ ዝግጅታቸዉን ያጠናቀቁ መዋቅሮች መኖራቸዉም አስረድተዉ ለአብነት ያህል ቡታጅራ ከተማ ለ27 ለተደራጁ ማህበራት ቦታ ማዘጋጀት የተቻለ ሲሆን በተመሳሳይ ሶዶ ወረዳም ላይ ለ4 ማህበራት ለማስተላለፍ ዝግጅታቸዉን ያጠናቀቁበት ሁኔታ መኖሩም ተናግረዋል።

በየደረጃው የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሰፊ ቅሬታ መኖሩ በመግለፅ በቀጣይም ያቀዱት የ90 ቀን እቅድ ለማሳካትና ህዝቡ ያነሳቸው የአገልግሎት አሰጣጥ፣በየከተማው የተጀመሩ መሰረተ ልማቶች የማጠናቀቅና ሌሎችም ችግሮች ለመፍታት የተጀመረው ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚናኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *