በእግር ኳስ ስፖርት በዳኝነት ሙያ ለተሰማሩ ሙያተኞች አቅማቸዉን በስልጠና በማሳደግ በዘርፉ የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

ለተከታታይ ሰባት ቀናቶች የሚቆይ የአንደኛ ደረጃ የእግር ኳስ የዳኝነት ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ዛሬ መስጠት ተጀምሯል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ አወል ጅማቶ ስልጠናዉ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት ስፖርት የሚመራዉ በእዉቀትና በክህሎት ሲሆን የባለሙያተኞች አቅም በስልጠና በመገንባት ሚዛናዊ ዳኝነት እንዲሰጡ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የእግር ኳስ የዳኝነት የስልጠና በተገቢዉ በመዉሰድ በዘርፉ ዉጤታማ ሆነዉ እንዲሰሩ ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ አወል የዳኝነት ስራ የህሊና ጉዳይ ሲሆን በዳኞች ስህተት በርካታ ችግሮች እንደሚፈጠርም አመላክተዉ በዳኝነት ወቅት የሚፈጠሩ ስህተቶች የሚቀረፉት ዳኞች በእዉቀትና በክህሎት እንዲገነቡ ማድረግ ሲቻል እንደሆነም አስረድተዋል።

ለተከታታይ 7 ቀናት የሚሰጠዉ የዳኝነት ስልጠና ሰልጣኞች በጥሩ ዲሲፒሊንና ስፖርታዊ ጨዋነት በመከተል በቆይታቸዉ የዳኝነት ሙያዉን የሚያግዛቸዉ የተሻለ እዉቀት ማግኘት እንዳለበቸዉ አሳስበዋል።

የሰልጣኞች የእያንዳዳቸዉ የግል ጥረት በማከልና በስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀት ተጠቅመዉ መዉደቅ እንደሌለበቸዉም አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደም ሽኩር በበኩላቸዉ የስፖርቱን ልማት ለማሳደግ በሚደረገዉ ጥረት በዞኑ ዉስጥ ያሉ በዳኝነት ሙያ የተሰማሩ ሙያተኞች አቅማቸዉን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነዉ።

ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆን ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነም አስታዉሰዉ የእግር ኳስ ስፖርት የማህበረሰብ አጠቃላይ ቀልብ የሚስብ የስፖርት አይነት ስለሆነ በዘርፉም የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩበት እንደሆንም ጠቁመዋል።

ሰልጣኞች የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጠና ከወሰዱ በኋላ በቀጣይ የፌዴራል ዳኝነት ስልጠና ዞኑ ባለዉ አቅም ልክ ስልጠናዎች የሚያገኙበት መድረኮች በማመቻቸት በዘርፍ ዉጤት እንዲመጣ እንደሚሰሩም አብራርተዋል።

በዘንድሮ አመት አጠቃላይ የስፖርት አይነቶቾ ዉድድር የተጀመረበት ሁኔታ መኖሩን አስታዉቀዉ ዉድድሩም የፌዴራልና የመጀመሪያ ደረጃ ስልጠና የወሰዱ ዳኞች ዉድድሩን ሲመሩበት የነበረበት ሁኔታ እንደነበረም አብራርተዋል።

ዛሬ የተጀመረዉ የአንደኛ ደረጃ የእግር ኳስ የዳኝነት ስልጠና በኮሚሽነር ቸሩ ጠበል አማካኝነት የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞች በትኩረት መከታተል ይኖርባቸዋል ብለዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *