በእዣ ወረዳ መንግስትና ህብረተሰቡ በመቀናጀት የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸው የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።


በእዣ ወረዳ መንግስትና ህብረተሰቡ በመቀናጀት የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸው የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

በወረዳው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ የእዣ ወረዳ አስተዳደር ገለጸ።

የጉራጌ ዞን የስራ ኃላፊዎች በእዣ ወረዳ በተለያዩ የስራ ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት በአርሶ አደሮች ጓሮ እየለሙ ያሉ ዝርያቸው የተሻሻሉ እና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የአቮካዶ እና የቡና ምርቶች የአርሶ አደሩ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በመሆናቸው አስፍተን ከሰራን ወደ ውጭ የመላክ አቅማችን ማሳደግ እንችላለን ብለዋል።

አርሶ አደሮች ጊዜውን ተረድተው እራሳቸው እንደባለሙያ ሆነው ሙከራ አድርገው፣ባህርዛፍ ነቅለው ጓሮዋቸው የፍራፍሬ ማሳ በማድረጋቸው ስልጡን መሆናቸው በተጨባጭ አስመስክረዋል ያሉት አቶ ላጫ የተጀመረው ጥምር ግብርና እንዲጠናከር አመላክቷል።

በኢንቨስትመንት እና በወጣቶች እየለሙ ያሉ የግብርና ስራዎች የአርሶ አደሩ ኑሮ እንዲሻሻል ከማድረጉ በተጨማሪ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና የአላቸው በመሆኑ የገበያ ትስስር በመፈጠሩ በዘርፉ ላሉት እጅግ ውጤታማ መሆን ችለዋል።

በተጨማሪ ቀጣይ ድህነትን ለመዋጋት የመኽር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው በወረዳው መንግስት በካፒታል ፕሮጀክት የሚሰሩ ግንባታዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በመሆናቸው አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገር ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

አቶ ላጫ አክለውም በእዣ ወረዳ በህብረተሰቡ፣በበጎ አድራጊዎች እና በመንግስት ቅንጅት በትምህርት ንቅናቄ የሚሰሩ ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸው እና ዛሬ ከታዩት ለአብነትም ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ በጥራት የተሰራው የዋዲየ ትምህርት ቤት ለሁሉም አረያ የሚሆን ነው ብለዋል።

በእዣ ወረዳ መንግስትና ህብረተሰቡ በመቀናጀት የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በጥራትም ሆነ በብዛት አበረታች በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት ህብረተሰቡ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የውጭና የውስጥ ሀይል ይበልጥም ባለሀብቱ በማስተባበር በርካታ ስራዎች ተሰርቷል።

በተለይ በመንገድ እና በትምህርት የተሰራው ስራ ውጤታማ ነው ያሉት አቶ ዘውዱ ህብረተሰቡ በማስተባበር በመንገድ እሰከ 50 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ ከ96 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መሰራቱ እና በትምህርት ንቅናቄ ደግሞ አበረታች ስራዎች እየተሰሩ እንሆነ አስገንዝበዋል።
በወረዳው ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በግብርና ዘርፉ በትኩረት እየተሰራ ሲሆን በሌማት ትሩፉት የፍራፍሬ፣የወተት፣የዶሮ፣የስጋ እና የማር መንደር ተፈጠሮ የህብረተሰቡ ኑሮ እየተሻሻለ መሆኑን ገልጸዋል።

በወረዳው ለካፒታል ፕሮጀክቶች ትኩረት በመስጠት ከ85 ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ የተለያዩ ግንባታዎች በፍጥነት እየተጠናቀቁ ሲሆን የመስኖና መሰል በፌደራል መንግስት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በመኖራቸው ቶሎ እንዲጠናቀቁ ከሚመለከተው አካል እነተነጋገርን ነው ብለዋል።

አቶ ዘውዱ አክለውም በእሻ ወረዳ ከ63 በላይ ኢንቨስትመንቶች መኖራቸው እና ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች መኖራቸው እንዲሁም ወረዳው ለኢንቨስትመንት ምቹ በመሆኑ ባለሀብቶች ገብተው እንዲያለሙ አስታውቀዋል።

በወረዳው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

አቶ አንዋር ሙዜ በወረዳው በኢንቨስትመን ዘርፍ ተሰማርቶ ድንችና መሰል ምርጥ ግብአቶች እያከፋፈለ የሚገኝ ሲሆን በሚሰራው የድንች ምርት ደግሞ ለሰን ቺብስ ድርጅት እና ለሌሎችም ምርቱን በመሸጥ ተጠቃሚ እየሆ መሆኑ ተናግሯል።

በዚህም በሄክታር እስከ 340 ኩንታል ምርት እንደሚያገኝ ጠቁሞ ከራሱ አልፎ ከ4ዐ0 በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ይናገራል።

በወረዳው በአቮካዶ እና በቡና ምርት የተሰማሩ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ድሮ ባህር ዛፍ ይተክሉበት የነበረ መሬት በመመንጠር አሁን ግን በአቮካዶ ተሞልቶ ተጨማሪ መሬት እየፈለግን እንገኛለን ብለዋል።

ለአብነትም በቅርቡ በአቮካዶ ምርት በአንድ ዙር 70 ሺ ብር እና ከዚያ በላይ መሸጥ የቻሉ ሲሆን በቀጣይ ምርቱን በማስፋት ለውጭ ሀገር ለመላክ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ አስገንዝበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *