በእውቀትና በጥሩ ስብዕና የታነፀ አንባቢ ትውልድ ለመገንባት የወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከላት በመጽሀፍት ማደራጀት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

ምሪያዉ የተለያዩ ይዘት ያላቸዉ መጽሀፍቶች በዞኑ ለሚገኙ ለ13 የወጣት ስብዕና ግንባታ ማዕከል የትምህርት ማጣቀሻ መጽሀፍት ድጋፍ አደረገ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ እንዳሉት በእውቀትና በጥሩ ስብዕና የታነፀ ትውልድ ለመገንባት የወጣቶች የንባብ ባህል ማጎልበት ይገባል፡፡

አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር የወጣቶች የስብዕና ግንባታ ማዕከላት በመጽሀፍት ለማደራጀት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኃፊው ይህን ተግባር ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሚና መጫወት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

በወጣት ማዕከላት ስብዕናዉን ያልተገነባ ወጣት ለራሱ ሆነ ለሀገር የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻር የሀገሪቱ ሰላም እንዳይረጋጋና የመንግስትን ስርዓት አደጋ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል፡፡ ለዚህ ማሳያ ደግሞ ከለውጡ በፊት የበነበረው የመንግስት ስርዓት የተገነባው ወጣት ለስብዕናው የማይጨነቅና ስም በማጠልሸት የተጠመደ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

የወጣት ስብዕና ግንባታ ማዕከሉ የህልዉና አደጋ ገጥሞት የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የዞኑ መንግስት በሚያደርግለት ልዩ ድጋፍ ማዕከላቱ እየተሻሻሉ መሆናቸው ገልጸዋል፡፡

በእዉቀት የዳበረና የተሻለ አንባቢ ትዉልድ ለመፍጠር የተለያዩ ለትምህርት አጋዥ የሚሆኑ መጽሀፍቶች ለ13 የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

ወጣቱ የነገይቱን ሀገር ተረካቢ እንዲሆን ለማስቻል በተለያዩ ጉዳዮች መንግስትን እንዲያግዙ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የዜጎች የማንበብ ባህል የተቀዛቀዘበት ወቅት እንደሆነም ያስረዱት አቶ አብዱ የንባብ ባህል እንዲዳብር ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበትም አመላክተዋል።

በዞኑ የሚገኙ ወጣቶች እንዲያነቡ በማድረግና የንባብ ባህል እንዲዳብር በማነሳሳት አንባቢና ተመራማሪ ትዉልድ መፍጠር እንደሚገባም አስታዉቀዋል።

የወጣቱና የማህበሰቡ የማንበብ ልምድ እንዲዳብር እንዲሁም ሁለንተናዊ ስብዕናን ለማጎልበት በወጣት ማዕከላት በተገቢዉ የተለያዩ ይዘት ያላቸዉ መጽሐፍት ማደራጀት ይገባል ብለዋል።

በዞኑ ለረጅም ጊዜ ተዘግተዉ የነበሩ የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በማስከፈትና በመጽሀፍትና በተለያዩ ቁሳቁሶች እንዲደራጁ በማድረግ በዘርፍ የተሻለ ዉጤት እንዲመጣ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈትጰቤት ኃላፊ አቶ አወቀ ገራቸዉ እና የቡኢ ከተማ አስተዳድር ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙለታ ነጋ በሰጡት አስተያየት የወጣቶች ስብዕና ለመገንባት አሁን ላይ በትኩረት እየሰሩ እንደሆነም አስረድተዋል።

ለማዕከላቸዉ አገልግሎት የሚዉል መጽሀፍት ለተደረገላቸዉ ድጋፍም አመስግነዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *