በእኖር ወረዳ ከ8.5 ሚሊየን ብር በላይ በማህበረሰቡና በባለሀብቱ ተሳትፎ የታተሙ የመመማሪያ መጽሀፍቶች እደላ እየተደረገ ይገኛል።

በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ አንድ መጽሀፍ ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ ቃል በተሰራው የንቅናቄ ስራ ታትመው የገቡ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሀፍ ለተማሪ ማሰራጫ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው።

መጸሀፍቶቹ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል የተማሪ የመማሪያ መጽሀፍቶች ሲሆኑ ከ20ሺ 50 በላይ መጽሀፍቶች በማህበረሰቡ እንዲሁም ባለሀብቱ በጋራ በመሆን ነው መጽሀፍቶቹ የታተሙት።

በዞኑ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ማህበረሰቡንና ባሀብቱን በማስተባበር 83 ሚሊየን 6መቶ 36ሺ 7መቶ ብር መጽሀፍት ለማሳተም እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ከ58ሺ በላይ መጽሀፍቶች ታትመው ተሰራጭቷል ተብሏል።

የትምህርት ስብራት ለመጠገን በሚደረገው ጥረት ማህበረሰቡ በግል ተነሳሽነት ለትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ለአብነትም ትምህርት ቤቶች በመገንባት፣መጻፍ የማሳተምና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው።

በፕሮግራሙ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አቶ መብራቴ ወ/ማረያም ጨምሮ የእኖር ወረዳ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *