በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች አርሶ አደሮች በኢኮኖሚውና በማህበራዊ ኑሮዋቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ ።

በአመቱ በተደረገው የዝርያ ማሻሻል ዘመቻ ከ9ሺ 8መቶ በላይ ጥጆችን መወለዳቸው መምሪያው አስታውቋል።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የእንሳት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሙደሲር በዓመቱ በመደበኛ፣በሰዉ ሰራሽ፣በተሻሻለ ኮርማ፣ እና በሲክሮናይዜሽን 21ሺ 1መቶ 60 ላሞችና ጊደሮች መዳቀላቸው ገልጸው 9ሺ 8መቶ 39 ክልስ ጥጆች ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

በዶሮ እርባታው ከ2 ሚሊዮን 80 ሺህ በላይ የ45 ቀን ቄብና ኮክኔ ዶሮዎች መሰራጨታቸው ገልጸዋል፡፡

እንደ መሀመድ ገለጻ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በአመቱ 9ሺ 2መቶ 78 ሄክታር መሬት በተሻሻለ መኖ ማልማት ተችሏል፡፡

ለዚህም ተግባር ጥቅም ላይ የዋሉ 5መቶ96 ነጥብ 9 ሚሊየን መኖ ችግኞች፣ የመኖ ዛፍ ችግኝ ፣የሳር ግንጣይ፣ ቁርጥራጭ ሳሮችና እንዲሁም 1ሺህ4 መቶ15 ኩንታል የመኖ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉ አመላክቷል።

ዘርፋ ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል መፍጠር ችሏል የሚሉት ኃላፊው 109ሺ 1መቶ 18 በሬዎች ማድለብ መቻሉ አስታውቀው ከ144ሺ በላይ የተሻሻሉ አውራ በጎችና ፍየሎች ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱ ገልጸዋል።

በዞኑ የአሳ ምርት እድገት አሳይቷል ያሉት አቶ መሀመድ ዘርፉን ለማሳደግ 11ሺ 200 የዓሳ ጫጩት ስርጭት ተከናውኗል ብለዋል፡፡

የእንስሳት በሽታን አስቀድሞ ለመከላከልና የጤና አገልግሎት ለመስጠት ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ፣ የውጭና የውስጥ ጥገኛ፣የገንዲ በሽታ፣የጡት በሽታ ለሌሎች በሽታዎች ህክምና መደረጉ ተናግሯል።

ለዚህ ደግሞ የዶዝ፣የሆሊስትን፣የጀርሲ የአባላዘር፣የፈሳሽ ናይትሮጅን ከተለያዩ የናይትሮጅን ማምረቻ ማዕከላት አቅርቦ ተሰራጭቷል ነው ያሉት።

በዚህም ከ3መቶ 56ሺ በላይ አ/አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል አቶ መሀመድ ሙደሲር፡፡

ጤንነቱ የተረጋገጠ ሥጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በዞኑ ውስጥ ባሉ ቄራዎች 51ሺ 6መቶ እንስሳቶች ላይ የቅድመና ድህረ እርድ ምርመራ አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

እንደ መሀመድ ገለጻ በስጋ ምርቶች እና በእንቁላል ምርት 33ሺህ 64 ቶን ምርት ሲገኝ በወተት ደግሞ 99ሺህ 1መቶ ቶን ምርት እንደተገኘ አመላክቷል ።

በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች አርሶ አደሮቹ በኢኮኖሚውና በማህበራዊ ኑሮዋቸው የበለጠ ተጠቃሚ መሆናቸው አቶ መሀመድ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን ተጭነው ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *