በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት በአገልግሎት አሰጣጡ ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ዉስንነቶች መቅረፍ እንደሚገባ ተገለጸ።

የግሉ ባለሀብት መሬት ለመቀበል በሚፈጥነዉ ልክ የተረከበውን መሬት ለማልማትም መፍጠን እንዳለበት በዞኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለጹ።

የዞኑን ሁለንተናዊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና የዘርፉ ችግሮች ለይቶ ለመፍታት የኢንቨስትመንት ፎረም በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።

በፎረሙ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አባስ መሀመድ እንዳሉት ኢንቨስትመንት ሳይኖር ብልጽግና ማሰብ አይቻልም ብለዉ ባለሀብቱ ፣መንግስትና ሰራተኛዉም ያለዉን ሀብትና እዉቀት አቀናጅቶ መስራት አለበት ብለዋል።

ባለሀብቱ ገንዘቡን እና ልምዱን ፣ ምሁሩ እዉቀቱን መንግስት ደግሞ መሬት በማቅረብ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ኢንቨስትመንት የወደፊት ገቢን ወይም ትርፍን ታሳቢ በማድረግ በአንድ ተቋም/ድርጅት/ ላይ የሚደረግ የገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀት የማፍሰስ ሂደት ነዉ።

ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በመጠን፣ በአይነትና በጥራት በማምረት የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ ምርት ለመተካት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የውጭ ምንዛሬን ለማዳንና በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ ለመጣው ስራ ፈላጊ ወጣት ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ እንደሆነም አመላክተዋል።

በሆቴል አገልግሎት ዘርፍ ለመሰማራት መሬት የወሰዱ ባለሀብቶች ደረጃቸዉን የጠበቁ ሆቴሎች ለመገንባት ፈጥነው ወደ ተግባር መግባት አለባቸው ያሉት አስተዳዳሪው ባለሀብቶች ደረጃዉን የጠበቀ ግንባታ ማያከናዉኑ ከሆነ እንደሚያስቆሟቸዉም አሳስበዋል።

ተከታታይነት ያለዉን ድጋፍና ክትትል በማድረግ መሬት ወሰደዉ በማያለሙ ባለሀብቶች እርምጃ ለመዉሰድ የተጀመረዉ ስራዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትር ልማትጨመምሪያ ሀላፊ አአቶ ናስር ሀሰን እንዳሉት በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚነሱ ችግሮች ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ዞኑ ለአልሚ ባለሀብቶች ምቹ እንደሆነም አንስተዉ መሬት ከተረከቡ ባለሀብቶች 35 በመቶ ብቻ ማልማት እንደተቻለም አስታዉሰዉ መሬት ወስደዉ ያላለሙ ባለሀብቶች እርምጃ የሚወሰድ እንደሆነም አመላክተዋል።

በመንግስት ቢሮች በኩል የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርና ፈጣን ምላሽ ያለመስጠት ችግሮች መኖሩም ተናግረዉ ይህንንም ችገር ለመቀረፍ አየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

በዞኑ ካሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ለ20 ሺህ 800 ቋሚና ለ22 ሺህ 496 ጊዚያዊ የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻሉም አብራርተዋል።

በፎረሙ የተገኙ አንዳንድ ባለሀብቶች በሰጡት አስተያየት በዞኑ ላይ በየትኛዉም የኢንቨሰትመንት ዘርፎች ብንሰማራ አዋጭ እንደሆነና ዉጤት ማምጣት እንደሚችሉም አመላክተዋል።

የዞኑ መንግስት በመሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚስተዋሉ ዉስንነቶች በመቅረፍ ባለሀብቶች በወሰዱት መሬት ዉጤታማ ስራ በመስራት ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንዳለባቸዉም ተናግረዋል።

ባለሀብቱ መሬት ለመቀበል እንደሚፈጥነዉ ሁሉ ለማልማትም መፍጠን እንዳለበት የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ከህብረተሰቡ ጋር ትስስር በመፍጠር በተሰማሩበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሻለ ስራ በመስራት ኢከኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ እንዳለበትም አመላክተዋል።

በመጨረሻም በዞኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች አልሚ የግሉ ባለሀብቶች ሰርተፍኬት እዉቅና ተሰጥቷቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *