የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊና ሀገራዊ ሁኔታው ላይ ዛሬ አስቸኳይ ውይይት በወልቂጤ ከተማ አካሄደዋል።
መድረኩን የመሩት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንደገለፁት ትህነግ ዛሬ ሀገር ለማፍረስ የጀመረው ሴራና ህልም ድንገት የተፈጠረ ሳይሆን ለ27 አመት ሲዘጋጅበት የቆየና ያደገበት ስልት ነው ።
በታሪካችን ኢትዮጵያ የትኛውም ያጋጠማት ፈተና በድል የተወጣች አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር ናት ያሉት አስተዳዳሪው አሁን ሀገር ከገጠማት ፈተና ለመታደግ የዞኑ አመራር፣ወጣቶችና መላው የዞን ህዝብ የማይከፍለው መሰዋአትነት አይኖርም ብለዋል።
ለዚህም የዞኑ ህዝብና አመራር መንግስት ላቀረበው የክተት ጥሪ መዝመት የሚችለው በመዝመት፣ሌላው በስንቅና ሞራል እንዲሁም ሁሉም ደግሞ አካባቢው ነቅቶ በመጠበቅ ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ በመድረኩ እንዳሉት ህዝባችን በተገቢ በማደራጀትና በመምራት ሀገር ለማፍረስ የተዘጋጀ አጥፊ ቡድን እንመክታለን ብለዋል።
የዞናችን ህዝብ ሀገር ችግር ውስጥ በገባችበት ጊዜ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ረገድ ግንባር ቀደም ነው ያሉት አቶ ክፍሌ ለማ ህዝቡ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሀገራዊ ጥሪው ፈጣን ምላሽ መስጠት አለበት ሲሉም ገልፀዋል።
በየደረጃው ያለው አመራር በተጠያቂነት ህዝቡን በተገቢ አደራጅቶ በመምራትና በማነቃነቅ ብሎም እስከ ግንባር በመዝመት ሀገር ለማፍረስ የታቀደ እቅድ ማምከንና የአካባቢው ሰላም ህዝቡን አሳትፎ ማስጠበቅ አለበት ብለዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮች እንደገፁት አመራሩና ህዝቡ ለየትኛውም ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ገልፀው በአጭር ጊዜ ወደ ተግባር እንሚቀየርና የፀጥታ አካላትን፣ወጣቱና ህዝቡ በማሳተፍ የካባቢያቸው ሰላም ለማስጠበቅ ዝግጁ ነን ሲሉ ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx