በአለም አቀፍ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ48ኛ ጊዜ የሚከበረዉ ማርች 8 ሴቶችን እናብቃ ሰላምና ልማት እናረጋግጥ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል ።

የካ

እለቱን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የአልባሳት ፣የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረግጎል።

የጉራጌ ዞን ሴቶች ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ነጅብያ መሀመድ እለቱን አስመልክተዉ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት በአሉ በዋናነት የሚከበረዉ በሴቶች ላይ ይደርሰ የነበረዉ ጭቆና ለማዉገዝ ፣ሴቶች በአደባባይ ቆመዉ ሀሳባቸዉ እንዲገልጹ ብቻ ሳይሆን እድል ካገኙ በየትኛዉም የሀገሪቱ እድገትና ለዉጥ ሊያፋጥኑ በሚችሉ ዘርፎች ከወንዶች ባልተናነሰ መልኩ በዉጤትና በስነ ምግባር የታጀበ ተግባር መፈጸም እንደሚችሉ አቅማቸዉን ለአለም ያስተዋወቁትን ለቀደምት ሴት ጀግኖች ትልቅ ክብርና ምስጋና አቅረበዋል።

በዛሬዉ ቀን የማርች 8( ኤይት) በአል ማክበር ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ጽኦታዊ ጥቃት ስር ያሉ ሴት እህቶቻችን የምንረዳበትና የምንደግፍበት እለት እንደሆነም አብራርተዋል።

የሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገዉ ባለዉ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በዞኑ 6 ሺህ 1መቶ 72 የሴቶች የልማት ቡድን መኖሩም ያመላከቱት ሀላፊዋ ከዚህ ዉስጥ 266 ሺህ 530 ሴቶች ተጠቃሚ እንደሆኑም ተናግረዉ ለነዚህም ከ47 ሚሊየን 532 ሺህ ብር በላይ ብድር የተመቻቸላቸዉና 115 ሚሊየን 282 ሺህ 710 ብር መቆጠባቸዉም አብራርተዋል።

ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ከ8መቶ ሺህ በላይ ሴቶች በሰላም ግንባታና በግጭት አፈታት ዙሪያ በሰላም ኮንፈረስ እንዲሳተፉ መደረጉም አስታዉሰዉ 15 ሺህ 108 ሴቶች ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ በሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራ መሰራቱም አስረድተዋል።

ጎዳና ላይ የሚጣሉና ኑሮአቸዉን ጎዳና ላይ ያደረጉና መሰል ችግሮች ያሉባቸዉ ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን ሚላዉ ማህበረሰብ ሊያግዛቸዉና ችግሩን ማቃለል እንዳለበትም ጠቁመዋል።

በተፈጥረና ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ችግር ለደረሰባቸዉ ከ10 ሺህ በላይ ሴቶችና ህጻናት የተለያዩ ድጋፎች መደረጉም አመላክተዉ 127 ሺህ 640 ሴቶች በተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሰማርተዉ ማህበረሰቡን በሚጠቅሙ ልማቶች እንዲሳተፉ መደረጉም ተናግረዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ የአካባቢዉን ሰላም በማስጠበቅ የሚታማ አንዳልሆነም አስታዉሰዉ ሁሉም ሰዉ ለሰላም እሴት ግንባታ ትኩረት መስትም እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወይዘሮ አመተረዉፍ ሁሴን እንዳሉት ሴቶች ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን መራር ትግል በማድረግ ረገድ የአንበሳዉ ድርሻ ተወጥተዋል።

ሴቶች በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ረገድ ትልቁን ድርሻ እየተወጡ እንደሆነም ጠቁመዉ ይህንንም መልካም ስራቸዉ የበለጠ አጠናክረዉ ሊሰሩበትም እንደሚገባም ተናግረዋል።

የዞኑ ሴቶች ከጥንት ጀምሮ ለለመብታቸዉና ለፍትህእኩልነት ከመታገል ጀምሮ ሀገር በማቅናትና ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫዉተዋል ብለዋል።

በመጨረሻም ለተለያዩ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ፣ የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረጓል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *