በነዳጅ ዋጋ ጭማሪና በሌሎችም ምክኒያቶች በማድረግ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ሲገጥሟቸዉ ለትራፊኮችና ለመንገድ ደህንነቶች ጥቆማ በመስጠት ለመብታቸውና ለህግ መከበር የበኩላቸው መወጣት እንዳለባቸዉም ተገለጸ።

በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከሀምሌ ወር ጀምሮ በየደረጃ ተሻሽሎ የመጣዉን ወቅታዊ ታሪፍ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸዉም የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አሳሰበ።

የታሪፍ ማሻሻያው አስመልክቶ የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ ባነጋገርንበት ወቅት እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ ዕቃዎች ንረትና የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዳለም ተናግረዋል።

ይህንን መነሻ በማድረግ የደቡብ ክልል በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ለዉጥ በማድረግ እስከታችኛዉ መዋቅር ድረስ እንዲወርድ መደረጉና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ እንደጀመሩም ተናግረዋል።

በዚህም በናፍጣ 8 ብር ከ60 በቤንዝል ደግ 6 ብር ገደማ በቴሌ ብር አማካኝነት የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩም አስታዉቀዉ የነዳጅ ድጎማዉ ደሀዉን ማህበረሰብ መሰረት ያደረገ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ለህዝብ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ድጎማ የሚደረግበት ዋነኛ ምክንያት ትራንስፖርት የሚጠቀመዉን ደሀዉ ማህበረሰብ በትክክለኛዉ ታሪፍ እንዲሳፈር ለማመቻቸት እንደሆነም አመላክተዋል።

በመሆኑም በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች ማለትም በተጠኑ መስመሮች አዲሱ የወጣዉን ታሪፍ ተጠቅሞ ባሉ መናሀሪዎች ገብቶ በወንበር ልክ በመጫን አገልግሎት ማግኘት አለበት ብለዋል።

አሽከርካሪዎች ተሳፋሪዎች ትክክለኛ ታሪፍ ከፍለዉ አገልግሎት እንዲያገኙና ለከፈሉት ብር ደረሰኝ በተገቢዉ መስጠት ይኖርባቸዋል ያሉት ኃላፊዋ ይህንን የማይተገብሩ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወሰድባቸዉ ህጋዊ እርምጃ የተጠናከረ መሆኑም አስረድተዋል።

ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ህብረተሰቡን በትክክለኛዉ ታሪፍ እንዲሳፈሩ ማድረግ ይገባል ብለዉ አሽከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማዉን ተጠቅመዉ የተስተካከለዉን ታሪፍ መተግበር ግዴታቸዉ እንደሆነም አሳስበዋል።

ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ከነዳጅ ድጎማዉ እስከ መሰረዝ ሊደርስ የሚችል እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉም ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ በየአካባቢዉ ባሉ መናኸሪያዎች ገብቶ በትክክለኛ በወንበር መጫን አለበት ብለዉ አሽከርካሪዎችም በመኪናቸዉ ለተሳፋሪዎች በሚታያቸዉ ቦታ ላይ ታሪፍ መለጠፍ እንዳለባቸዉምና ተሴፋሪዉም ለከፈለዉን ብር ደረሰኝ መቀበል እንዳለበትም አስረድተዋል።

ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽርካሪዎች ሲገጥሟቸዉ ለትራፊኮችና ለመንገድ ደህንነቶች ጥቆማ መስጠት ለመብታቸውና ለህግ መከበር የበኩላቸው መወጣት እንዳለባቸዉም አሳስበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *