በችግር ውስጥ ያሉትን አርጋውያን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ በተግባር ወገንተኝነታችን ማሳየት እንደሚያስፈልግ ተጠቁመዋል!

ነሀሴ 14/2014 ዓ.ም

በችግር ውስጥ ያሉትን አርጋውያን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ በተግባር ወገንተኝነታችን ማሳየት እንደሚያስፈልግ ተጠቁመዋል!

በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ገሬኖ እንሰት ተክል ቀበሌ ረዳትና ጠዋሪ ለሌላቸው በእድሜ ለገፉት አባት የወረዳው ወጣት አደረጃጀት አዲስ ቤት ሠርቶ በማስረገብ የበጎነት ተግባሩ ቀጥሎበታል።

የሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሳይ ገዛኻኝ በዚህ አቀመ ዳካማ ወገኖችን የማገዝ ተግባር የሶዶ ወረዳ የወጣቶች አደረጃጀቶች በተለያዩ ቀበሌዎች ስናገዝ እንደመጣነው ዛሬ በገሬኖ እንሰት ተክል ቀበሌ የዘንድሮ ክረምት በጎፈቃደኞች አዲስ የመኖሪያ ቤት በመስራት የአንድ ረዳት የሌላቸው አባት የቤት ችግር መቅረፍ እንደተቻለ ገልፀዋል።

እንደዛሬው አባት ድጋፍ የሚሹ በርካታ ወገኖች መኖራቸውን ጠቁመው የእነዚን ህይወት መታደግ በመንግስት ብቻ ተደራሽ ማድረግ ስለሚያስቸግር መሠል በጎ ተግባራት በማስፋት ያለው በገንዘቡ የሌለው በጉልበቱና በሀሳብ በመደገፍ ለወገን አለኝተነታችን በተግባር ማሳየት ይገባናል ነው ያሉት።

የሶዶ ወረዳ ወጣቶች ፌድሬሽን ሰብሳቢ አቶ ከበደ ብሩ እንዳስረዱት የክረምት በጎ ፈቃድ ከተጀመረ 13ኛው አዲስ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ያደረጉበት መሆኑን በዚህ በጎ ተግባር ወጣቱ ከአካባቢው ማህበረሰቡን ጋር በመተባበር እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህ የሰብዓዊነት ተግባር ማስፈፀሚያ ገንዘብ የሚገኘው ከፈቃደኛ ወጣቶችና ባለሀብቶች እንዲሁም ካላቸው ከሚያካፍሉ ደጋጎች እንደተገኘ ገለጸው ሆኖሞ የወረዳው ወጣት አደረጃጀት ብቻውን ዕቅዱን ለማሳካት ስለማይችል በአንዳንድ ቀበሌዎች የወጣቶች የበጎ ፈቃደኞች ሠራዊት የማፍራት ክፍተት በማረም መሠራት እንዳለበት አመላክተዋል።

የሶዶ ወረዳ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወይዘሪት ወርቅአበባ ኦረሞ ሴቶች አደረጃጀቶች ከሌሎች ወጣት አደረጃጀቶች ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ ሲሰሩ መቆየታቸውና እንደዛሬው በባሰ ችግር ውስጥ ያሉትን አርጋውያን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ በተግባር አለንላችሁ በማለት ወገንተኝነታችን በማሳየት አርአያነቱን ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

የገሬኖ እንሰት ተክል የወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ የሆነው ወጣት አቡ አሰፋ እንደገለፀው ዛሬ የመኖሪያ ቤታቸው በመፍረሱ ምክንያት በሰው ቤት ለመጠለል የተገደዱት አቶ ማስረሻ ዘለቀ የተባሉት በእድሜ የገፉት አባት በሶዶ ወረዳ ወጣቶች አስተባባሪነት የቀበሌው አስተዳደርና ወጣቶች ተባባሪነት በጋራ አዲስ ቤት እየሠራን እንገኛለን ብሏል።

ቀሪ ሥራዎቹም ጭቃ የመለጠፍ፣ የማሳመር፣ አስፈላጊው የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ገዝቶ ለመስጠት የሴቶች አደረጃጀት በመጠቀም ለቤት ወለል የሚያስፈልገው ለመኝታም ጭምር የሚያገለግሉትን በሙሉ ለማሟላት አቅደው እየሠሩ እንደሚገኙ መናገራቸውን ከሶዶ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መረጃዎቻችበተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *