በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለዉን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ እንደሆነም የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የትራንስፖርት የቁጥጥር ስራዉ አጠናክሮ በማስቀጠል፣ህገ ወጥ ደላሎች በመከላከልና በትክክለኛ ታሪፍና በወንበር ልክ ተሳፋሪ በመጫን የትራንስፖርት ህጉን በተገቢዉ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ተብለዋል።

መምሪያው የትራንስፖርት ዘርፉ ችግሮች ለመፍታትና የህዝቡ ቅሬታ ለመቀነስ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች ከተዉጣጡ አመራሮችና ባለድርሻ አካላቶች በወልቂጤ ከተማ ተወያይተዋል።

የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንዳሉት የትራንስፖርት ዘርፍ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለበትምና ሰፊ የህዝብ እሮሮ የሚደመጥበት መሆኑ ገልፀው ችግሩ ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል።

አሽከርካሪዎች ከታሪፍ በላይ በማስከፈል፣ ከተፈቀደላቸዉ በላይ ትርፍ ሰዉ በመጫን ረገድ ትልቅ ችግር የሚስተዋል ሲሆን ይህንንም ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል።

የጉራጌ ህዝብ እንደማንኛዉም ህዝብ ክብር የሚገባዉ ነው ብለው ሀላፊዋ በትራንስፖርቱ ዘርፍ የሚሰተዋለዉን ችግር ሊበቃ እንደሚገባና የህዝብ ተሽከርካሪዎች በትክክለኛ ታሪፍ በማስከፈልና የተፈቀደላቸዉ ሰዉ በመናኸሪያ ውስጥ እንዲጭኑ ለማድረግ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላቶች ቅንጅታዊ ስራ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል።

ዘርፉ ከፍተኛ ኪራይ የሚስተዋልበትና ጫናው ደግሞ ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ማማረሩን ገልፀው ከችግሩ ለመሻገር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

ሀላፊዋ አክለዉም በትራንስፖርት ዘርፉ የሚስተዋለዉን የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ቅሬታ ለመቅረፍ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ሊጠናከርና በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጀማል አብድላ በዉይይቱ ወቅት ተገኝተዉ እንዳሉት በትራንስፖርት ዘርፉ ሰፊ የሆኑ ችግሮች ያሉበት ሲሆን ትርፍ በመጫንና ከታሪፍ በላይ በማስከፈል እንዲሁም ተሽከርካሪዎች ካለ መስመር በመንቀሳቀስና ከመናኸሪያ ውጭ በመጫን በህብረተሰቡ ላይ ብዙ ቅሬታዎች እየተነሳ እንደሆነም አስረድተዋል።

ችግሮቹን ለመፍታት ፖሊስ፣ ከመንገድ ደህንነትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላቶች ጋር በመቀናጀት የትራንስፖርቱ ዘርፍ ከችግር እንዲወጣ መሰራት እንዳለበትም አብራርተዋል።

በዞናችን በርካታ አካባቢዎች በትራንስፖርት ህገወጥ ድርጊቶች መኖራቸዉም አስረድተዉ ይህንንም ለማስቆም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተዉ መስራት እንዳለባቸዉም አስታዉቀዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት በትራንስፖርት ዘርፍ ህግ ለማስከበር በተለያዩ ጊዜያት ይሞከር እንደነበርም አስታዉሰዉ አሁንም ህጉ በተገቢዉ ማይተገብሩና ህግ የሚጥሱ ተሽከርካሪዎች ለማስቆም የመንገድ ደህንነቶች ፣ የትራፊክ ፖሊስና የህብረተሰቡ ሚና የጎላ እንደሆነም አመላክተዋል።

የትራንስፖርት የቁጥጥር ስራዉ ላይ መላላት የሚስተዋልበትና ህዝቡን የሚያማርር ከታሪፍ በላይ የማስከፈልና ትርፍ የመጫን ሁኔታዎች የሚስተዋሉ እንደሆነም አብራርተዉ በቀጣይ እነዚህ ችግሮችን ለመቅረፍ ዘርፉ ላይ አበክረዉ እንደሚሰሩም አስታዉቀዋል።

በመድረኩም የዞኑ ምክርቤት የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴዎች፣የሁሉም ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች የመንገድ ደህንነት ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አዛዦች ፣ የትራፊክ ፖሊሶችና አዛዦች ፣እንዲሁም የመምሪያዉ የማኔጅመንት አባላቶችና ሌሎችም የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *