በትራንስፖርት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

በዞን በሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች አዲስ የወጣዉ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንዳሉት መንግስት ከወቅቱ የነዳጅ አቅርቦት ጋር ተያይዞ በትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ማድረጉም የሚታወቅ ሲሆን አዲስ የወጣዉ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ ግብረሐይል ተዋቅሮ በትኩረት እየተሰራ ነው።

ሆኖም እንደ ሀገር ከሰሞኑ በተደረገ የቤንዚንና የናፍጣ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ አሽከርካሪዎች ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በህብረተሰቡ ላይ እያደረጉ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

የአስፖልትና የጠጠር መንገዶች ላይ አዲስ በወጣዉ የታሪፍ ማሻሻያ ልዩነት እንዳላቸዉም የተናገሩት ኃላፊዋ ይሁን እንጂ ማስተካከያውን ተከትሎ በመንግስት ከተቀመጠው የትራንስፖርት ታሪፍ ውጭ ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አሽከርካሪዎች መኖራቸውና ከድርጊታቸዉም ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመንግስት ከተቀመጠው የትራንስፖርት ታሪፍ ውጭ ያልተገባ ዋጋ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ የተጀመረው እርምጃና ህግ ማስከበር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የደረጃ 1፣ የደረጃ 2 እንዲሁም የደረጃ 3 ተሽካሪዎች ላይ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ የተደረገባቸዉ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ ፅ/ቤቶችም ማሻሻያው መሠረት በማድረግ የአካባቢ መዳረሻዎች ታሪፍ በማሳወቅ እተሰራ ሲሆን መላዉ ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉትን ጥቆማ በመስጠትና በመከላከል የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ቀልጣፋና ዉጤታማ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠትና በዘርፉ የሚስተዋለውን የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች አጽንዕኦት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *