በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ያሉ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን በአግባቡ በመወጣት ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባ የበቀለ አብሽሮ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አስታወቀ።

ጷግሜ 2/2014

በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ያሉ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን በአግባቡ በመወጣት ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባ የበቀለ አብሽሮ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አስታወቀ።

በቀለ አብሽሮ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት በቡታጅራ ከተማ የጨርቃ ጨርቅና ልብስ ስፌት ኢንዱስትሪ በማቋቋም ደስታ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እህት ኩባንያ ከ850 በላይ ለሚሆኑ ለቡታጅራና አካባቢው ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ለአካባቢው ብሎም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ጉልህ ሚና እየተወጣ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ተደራሽ ለማድረግ ከምስራቅ መስቃን ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ጋር በመነጋገር በወረዳው በኢሌ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ ከ850 ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የእናቶች ማቆያ ለመገንባት የቦታ ርክክብ ተደርጓል።

በጨርቃ ጨርቅና ልብስ ስፌት ድርጅቱ የፋብሪካና ፕሮጀክት አስተዳደር ኃላፊ አቶ ያሬድ ወልዴ እንደገለፁት ድርጅታቸው በተለይም በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ያሉ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን በአግባቡ ለመወጣት በተለያዩ ወረዳና ከተማ አካባቢዎች በርካታ ስራዎች እየሰራ ነው።

በዛሬው እለትም አቶ ያሬድ በምስራቅ መስቃን ወረዳ በኢሌ ቀበሌ ጤና ጣቢያ የወላድ እናቶችን ችግር በሚገባ መቅረፍ የሚችል የእናቶች ማቆያ ክፍሎችን መገንቢያ የሚሆን ቦታ ከወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ ርክክብ አድርገዋል።

የእናቶች ማቆያ ግንባታው ከ850 ሺ ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበት የጠቆሙት ኃላፊው በቅርቡ የግንባታው ሙሉ ወጪ ሸፍነው በማጠናቀቅና ለአገልግሎት ዝግጁ በማድረግ እንደሚያስረክቡና በቡታጅራ ከተማ የጨርቃ ጨርቅና ልብስ ስፌት ድርጅታቸው ለሚያስገነባው የአብሽሮ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም እንዲሰየም ተናግረዋል።

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ በበኩላቸው የቦታ ርክክብ በፈፀሙበት ወቅት እንደገለፁት ይህ ሀገር በቀል ድርጅት በጤናው፣ በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በቀጣይም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።

በተለይም ለመገንባት የታሰበው የእናቶች ማቆያ እናቶች በሚወልዱበት ወቅት በወሊድ ምክንያት የእናቶችና ህፃናት ስቃይና እንዲሁም ሞትን በከፍተኛ ሁኔታ አንደሚቀርፍ ገልፀው ላደረጉት አስተዋፅኦም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል ሲል የምስራቅ መስቃን ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት አድርሶናል።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *