በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት የሚሠጡ ስልጠናዎች ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የቡኢ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ገለፀ።

ጷጉሜ 4/2014
በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት የሚሠጡ ስልጠናዎች ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የቡኢ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ገለፀ።

ኮሌጁ በ2014 ዓ.ም አፈፃፀም ወቅት ባጋጠሙ ችግሮችና በቀጣይ ዓመት የስልጠና ዝግጅት ዙሪያ ከቦርድ አመራር አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ይሽልጌታ በላይነህ በዚህ ወቅት እንደገፁት ኮሌጁ የአካባቢው ማህበረሰብ ችግር ፈቺ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠርና ማሻሻል የሚችል ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ተልኮውን በአግባቡ መወጣት እንዲችል የቦርድ አባላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት የሚሠጡ ስልጠናዎች ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ኃላፊው አመላክተዋል።

ኮሌጁ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር የጀመራቸውን መልካም ጅምሮችን በማጠናከር በቀጣይ ለኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር ለተጠቃሚው ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

የመደበኛና የአጫጭር ሰልጣኞች ቁጥር ለማሳደግ ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት የኮሌጁን የስራ ውጤታማነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱ አህመድ ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ብቃት ያላቸዉ ሰልጣኞችን በማፍራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት የቦርድ አባላትና ባለድርሻ አካላትን በተገቢው አሳትፎ በጋራ መረባረብ ይጠይቃል ብለዋል።

የተሻሻለ አሰራር በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲችሉ በተለያዩ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ለመደገፍ እየተደረገ ያለው ጥረት በማጠናከር ብቃታቸውን በምዘና በማረጋገጥ ተወዳዳሪ ከማድረግ አንጻር የሚስተዋሉ ውስንነቶች ሊቀረፍ ይገባል ነው ያሉት።

የሠልጣኝ ተማሪዎች ቅበላ አቅሙን በማሳደግ በመካከለኛና በዝቅተኛ ደረጃ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰዉ ሀይል ለማፍራት በቀጣይ ተጠቃሚውን ማህበረሰብ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቡኢ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ሙሉጌታ ሞላ ኮሌጁ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማፍራት ረገድ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት እንዳይወጣ በሚያጋጥሙት ችግሮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይም ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።
የአካባቢው ማህበረሰብ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ የበቆሎ መፈልፈያ ፣ ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤትና የእንጨት መሠንጠቂያ ማሽን በመስራት ውጤታማነታቸውን በማረጋገጥ ለኢንተርፕራይዞች በማስተላለፍ ለተጠቃሚው ተደራሽ የማድረግ ስራ አንሚሰራ ገልፀዋል ።

ኮሌጁ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በዘንድሮ ደረጃ ለአረጋውያንና የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ፣የቤት ክዳን ቆርቆሮ መግዣና ሌሎችም የበጎ ፈቃድ ስራ በመስራት ከ43ሺ ብር በላይ ማበርከታቸውም ተናግሯል ።

የአረንጓዴ ልማት ስራ በተሻለ መልኩ በመስራት ግቢውን ውብና ማራኪ በማድረግ የመማርና የማስተማሩ ሂዲት ምቹ እንዲሆን የኮሌጁ ግንባታ በወቅቱ አለመጠናቀቁ ማነቆ ሆናል ሲሉ ገልፀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮሌጁ በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረውና ያጋጠሙ ችግሮች ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *