በተማሪዎች መካከል የሚደረጉ የጥያቄና መልስ ዉድድር ጤናማ የፉክክር መንፈስ በመፍጠር የተማሪዎች ዉጤት እንዲሻሻል አይነተኛ ሚና እንዳለዉ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

በተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ፍክክር የታየበት ዞናዊ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ዉድድር በወልቂጤ ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።

ዞን አቀፍ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ዉድድሩን ያስጀመሩት ጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንዳሉት የጥያቄና መልስ ዉድድሩ በ9ኛ እና የ11ኛ ክፍል በየወረዳና ከተማ አስተዳደር አሸናፊ ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ዉድድር ነዉ።

በዞናች የተማሪዎች ዉጤትና ስነ ምግባር ከፍተኛ ችግር መኖሩን አስታዉሰዉ በባለፉት አመታት የ8ኛ ክፍል ክልላዊና የ12ኛክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ የዉጤት መቀነስ እየተስተዋለ ይገኛል ።

ይህንን ዉጤት ለማስተካከል በርካታ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነም አስታዉቀዉ ዞናዊ የጥያቄና መልስ ዉድድር ማካሄድ አንዱ እንደሆነና ውድድሮች በተማሪዎችና ትምህርትቤቶች እንዲሁም በወረዳና ከተሞች መሀከል ተካሄዷል።

ዉድድሩም ተማሪዎች ለቀጣይ ክፍተታቸው አውቀው እንዲዘጋጁ፣ እርስ በእርሳቸዉ ልምድ እንዲለዋወጡና የፉክክር መንፈስ በተማሪዎች መካከል የሚፈጥር እንደሆነም አስታዉቀዋል።

በመጀመሪያ መንፈቅ አመት በዞኑ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዞናዊ ፈተና በማዘጋጀት ተማሪዎች እንዲፈተኑ መደረጉም አስታዉሰዉ በዞኑ የሚዘጋጁ ጥያቄዎች ለክልልና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚያዘጋጅና በስታንዳርዱን መሰረት የተዘጋጀ ጥያቄ እንደሆነም አብራርተዋል።

በተማሪዎች በየትምህርት አይነቱ ያለባቸዉ ጉድለቶችን ሊሞላ የሚችል ድጋፍና ክትትልም ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነም አስታዉቀዉ በየትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚስተዋል የመዘናጋት ችግር መፍታት የሚቻለዉ መሰል ዉድድሮች በማዘጋጀትና በማነሳሳት እንደሆነም አብራርተዋል።

በውድድሩ የወልቂጤ ከተማ የሚገኙ ግንባር ቀደም ተማሪዎች እንዲካፈሉ መደረጉም አብራርተዉ ከዉድድሩ ልምድ ወስደዉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ተማሪዎች ለማፍራት አጋዥ እንደሆነም አስረድተዉ ይህ ተግባር ቀጣይነት እንዳለዉም ተናግረዋል።

ተማሪ መኑር ይብጌታ፣ተማሪ አሻግሬ ነጋ፣ተማሪ እየሩስአለም አስፋ በጋራ በሰጡት አስተያየት የጥያቄና መልስ ዉድድሩም ጥሩ ፉክክር የታየበትና ለቀጣይ ልምድ የቀሰሙበት እንደሆነና ተማሪዎች እንዳይዘናጉ የሚያደርግ እንደሆነም ተናግረዋል።

በዉድድሩም ከ9ኛ ክፍል 1ኛ በላይነህ አሰፋ እኖር ኤነር ወረዳ ፣ 2ኛ አብድልሰላም ሀብታሙ፣3ኛ ተማሪ ታምራት ስራኒ ዉድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።

በ11ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ 1ኛ አሻግሬ ነጋ ቡኢ ከተማ አስተዳደር ፣ 2ኛ ቅድስት እንዳለ ከወልቂጤ ከተማ ፣3ኛ መኑር ይብጌታ ከጌታ ወረዳ ዉድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።

በ11ኛ ክፍል በማህበራዊ ሳይንስ 1ኛ ዳዊት ካሳ ከምስራቅ መስቃን ወረዳ፣2ኛ ክሩቤል ጸጋዬ ሙህርና አክሊል ወረዳ እንዲሁም 3ኛ እየሩሳሌም አሰፋ ከእዣ ወረዳ በመሆን ዉድድራቸዉን አጠናቀዋል።

በመድረኩ በዞኑ በ2013 አመተ ምህረት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ዉጤት ያመጡ ተማሪዎች ተገኝተው ልምዳቸዉን ለተማሪዎች አካፍለዋል ።

በመጨረሻም የጥያቄና መልስ ዉድድሩን በበላይነት ላጠናቀቁ ተማሪዎች የሰርተፍኬትና የገንዘብ ማረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *