በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚስተዋሉ የአሰልጣኞች የአቅም ውስንነትን በመቅረፍ በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ውጤታማ ስራ ለመስራት ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽዕኖት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን የስፖርት ባለሞያዎችና የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎችን የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኞች ስልጠና በወልቂጤ የኒቨርሲቲ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን መስጠት ተጀምረዋል። ዩኒቨርስቲው ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የስፖርት ልማት ዘርፉን ለማስፋፋትና ለመደገፍ በቅርበት ይሰራል። የጉራጌ ዞን ወጣቶችና እስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር በስልጠናው ማስጀመሪያ ወቀት እንደገለጹት መምሪያዉ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሶስት የስፖርት አይነቶች በአትሌቲክስ፣በቅርጫት ኳስና በቮሊቦል የስፖርት አይነቶች የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኞች ስልጠና ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንት እንደሚሰጥም ተናግረዋል። ስልጠናው ያስፈለገበት ዋናው አላማ ዞኑን በሁሉም የስፖርት አይነቶ ተሳታፊ ለማድረግና የአሰልጣኞች የአቅም ውስንነት በመቅረፍና በስፖርት ዘርፎች አመረቂ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሆነም ገልጸዋል ። አቶ አደም ሽኩር አክለውም በእውቀት የዳበር አሰልጣኞችን በማፍራት ታዳጊ ስፖርተኞችን ታች ወረዶ በማሰልጠንና በማብቃት በሀገር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትኩርት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል ። የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብቴ ዱላ በስልጠናው ማስጀመሪያ ወቅት እንዳሉት ሰልጣኞች በንድፈ ሀሳብ ያገኟቸውን እውቀቶች ወደ ተግባር የሚቀይሩበትና ትልቅ አቅም የሚያገኙበት እንደሆነም አስታዉቀዋል። ስልጠናው ለተከታታይ 15 ቀን እንደሚቆይና ሰልጣኞች በቆይታቸው የሚጠበቅባቸውን እውቀት በመቅሰም በዘርፉ የሚስተዋለዉን ችግር መቅረፍ እንደሚገባቸዉም አሳስበዋል። የዩኒቨርሲቲዉ የስፖርት ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶከተር አብዱላዚዝ ሙሰማ በበኩላቸዉ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በቅንጅት በመሆን በስፖርቱ ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየቱም ተናግረዋል። በተጨማሪም ዩኒቨርስቲው ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን የስፖርት ልማት ዘርፍን ለማስፋፋትና ለመደገፍ በቅርበት እንደሚሰራም ተናግረዋል ። በዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የሚገኙ መዋቅሮች በእያንዳንዱ የስፖርት አይነት የተውጣጡ አሰልጣኞች፣ክለቦች ውስጥ ያሉ ስፖርተኞችና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ተማሪች በስልጠናው እየተሳተፉ ይገኛል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን! = ኢትዮጵያን እናልማ! = የፈረሰውን እንገንባ! = ለፈተና እንዘጋጅ! በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡ Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone Website:- https://gurage.gov.et Telegram:- https://t.me/comminuca Youtub: –https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *