በቡታጅራ ከተማ የሚገኘው የግራር ቤት ተሃድሶ ሆስፒታል በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት 1ሺ ክራንች ድጋፍ አደረገ ፡፡

የድርጅቱ ም/ዳይሬክተር እና የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ተሾመ ቱሉ ፣ ለጀግና የሰራዊት አባላቶች የበኩላቸውን በመወጣታቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና ነዋሪነታቸው በካሊፎርኒያ ቢኤርያ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን 130ሺ ብር የሚገመት የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እና የውስጥ ልብስ ድጋፍ አድርገዋል ፡፡

ድጋፍ አድራጊዎቹን በመወከል ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ ገነት አበበ ፣ እኛ ይህንን ድጋፍ የሰበሰብነው ከዘመድ ጓደኞቻችን ትንሽ ትንሽ በማድረግ ነው፡፡ ማንም ሰው ጀግኖቻችንን ልርዳ ብሎ ካሰበ የድጋፍ መጠኑ አነሰ በዛ የሚለው ጉዳይ ሳያስጨንቀው ቀርቦ ሊጠይቃቸው ይገባል ብለዋል።

የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ብ/ጀ ዘላለም ፈተና ፣ ከዚህ በፊትም ሆነ በዛሬው እለት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ሁሉ ታላቅ ምስጋና በማቅረብ ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልእክት ማስተላለፋቸው ከኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *