በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የዞኑ የአርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያስቻላቸው መሆኑ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የመስክ ጉብኝት ተደረገ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንዳሉት አርሶ አደሩ የግብርና ባለሙያና አመራሩ የሚሰጠው እውቀት ተቀብሎ በመስራቱ በዞኑ ብሎም እንደ ክልልም ግንባር ቀደም ስራ መሰራቱ አመላክቷል።

በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የዞኑ አርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያስቻላቸው መሆኑ የተናገሩት አቶ መሀመድ ቀጣይ ምርቱ ተሰብስቦ ጎተራ እስከሚገባ ድረስ ክትትል ይፈልጋል ብለዋል።

ቀጣይ እንዲህ አይነት የግብርና ስራዎች ለመስራት ያሉን ውስን የመሬት ሀብቶቻችን በመጠቀም አርሶ አደሩ፣ ወጣቶችና ሴቶች መለየትና ማሳተፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

መንግስት የአርሶ አደሩ የልማት ጥያቄ ለመመለስ የአቅም ውስንነት በመስተዋሉ አርሶ አደሩ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች በፍትሀዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል አቶ መሀመድ ጀማል።

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም እንዳሉት የውሃ አማራጮች በመጠቀም በተመረጡ 5 ቀበሌዎች 31 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር በመገባቱ 31 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን አብራርተዋል።

በዚህም ከ2000 ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የተናገሩት አቶ ሸምሱ እስከ ምርት አሰባሰብ ድረስ ድጋፍና ክትትሉ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

አርሶ አደር ዳውድ ኤሰቦ እና ዲኖ ሁሴን በሀደሮ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ አምራች አርሶአደሮች ናቸው።በአካባቢው ያለው ውሃ ተጠቅምው መስኖን በመስራታቸው እጅግ ተስፋ ሰጪ ስራ ይታያል ብለዋል።

ሁሉም አርሶ አደሮች አሳታፊ እንዲሆንና በቀበሌው መስኖን በስፋት ለመጠቀም የውሃ ታንከር ጨምሮ ዘመናዊ የግብርና ግብአቶች እንዲሟላላቸው ጠይቀዋል።

በጉብኝቱ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አርሺያ አህመድ፣የዞኑ ምክትል አስተዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ፣ የዞኑና የወረዳው አመራሮች የአካባቢው ህብረተሰብ ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36C

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *