በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የአርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ተግባር ከመሆኑም በሻገር ከውጭ የሚገባውን እርዳታ ማስቀረት እንደሚችል የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳደር ገለጸ ።

በበጋ መስኖ ስንዴ እና በመደበኛ መስኖ 3 ሺህ 5 መቶ 97 ሄክታር መሬት መልማቱም ተግልጿል።

የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር በመስክ ጉብኝቱ ላይ እንዳሉት የውኃ አማራጮችን በማስፋትና የማህበረሰቡን የክህሎት አቅም በማዳበር እንደ ሀገር የተያዘውን ከውጭ የሚመጣን ስንዴ በራስ አቅም የመተካት እቅድ እውን ለማድረግ ያስችላል ።

ዘንድሮ የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴና መደበኛ መስኖው ልማት ለወረዳው ብሎም እንደ ሀገር ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም እንደሚፈጥርና ለዚህም መሳካት የወረዳው አመራር፣የዘርፉ ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል ።

በተጨማሪም ወረዳው ባመቻቸው የገንዘብ ብድርና የተለያዩ የግበአት አቅርቦት እንዳይገጥማቸውና የአርሶ አደሩን ችግር ለመቅርፍ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ይልማ እንደገለጹት በአመት ሁለቴና ከዛ በላይ በማምረት ምርትና ምርታማነትን በማሳዳግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

በበጋ መስኖ ስንዴ እና በመደበኛ መስኖ በአጠቃላይ 3 ሺህ 5 መቶ 97 ሄክታር በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ የለማ ሲሆን ከ97 ሄክታር በላይ የሚሆነው ስንዴ እነደሆነም ኃላፊው ጠቁመዋል ።

አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በቀጥታ ወደ ገበያ የሚያቀርብበት መንገድ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካለት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነና ለዋጋ ንረቱም መረጋጋት ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ተናግረዋል ።

ሁሉንም የግብርና ተግባራቶች አቀናጅቶ በመምራትና ውጤታማነትን በማሳደግ ከዘረፉ የሚጠበቀውን ውጤት ለማሳካት ባለድርሻ አካላትና ማህበረሰቡ በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል ።

በወድሮ ቀበሌ በልማት ቡድንና በማህበር ተደራጅተው ሲሰሩ ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች የበጋ ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ እያለሙ መሆናቸውን አብራርተዋል ።

ለበርካታ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል እንደፈጠሩና ቀጣይ ወደ ኢንቨስትመንት ለመሸጋገር አቅም እንዳላቸውና ለዚህ የወረዳው ድጋፍና ክትትል ወደር የሌለው መሆኑን ገልጸዋል ።

በበጋ ስንዴ እና በመደበኛ መስኖ የለማ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራዎች የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር፣ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ይልማ፣የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የግብርና ባለሙያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ወድሮና ባካንወቴ ቀበሌ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ፣ የፈረሰውን እንገንባ፣ለፈተና እንዘጋጅ!

በመረጃ ምንጭነት ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *