በበልግ እርሻ ልማት በ5ቱ ዋና ዋና ሰብሎች 3ሺህ 927 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ገለፀ።

ምንም እንኳ የዝናብ እጥረት ቢከሰትም በማሳቸው ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ በአግባቡ በመስራታቸው የከፋ ጉዳት እንዳያመጣ እንደጠቀማቸው ያነጋገርናቸው አንዳንዳ አርሶአደሮች ተናግረዋል ።

የእዣ ወረዳው የግብርና ልማት ፅ/ቤት ም/ሀላፊና የእርሻ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ተካ ወርቁ እንደገለፁት የበልግ ልማት ከወረዳው የመልማት አቅም አንፃር የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥ በመሆኑ እንደ ወረዳው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል ።

ምክትል ሀላፊውም ጨምረው እንገለፁት ከበልግ ሰብል ልማት ጎን ለጎን የተቀናጀ የመኖ ልማት ስራን በማጠናከርና የእንሰሳትን ምርታማነት የማረጋገጥ ተግባራትን በተጨማሪ የፍራፍሬ ልማትም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል ።

በወረዳው በ2014 ዓም በልግ ልማት 3 ሺህ 927 ለማልማት ታቅዶ በ5ዋና ዋና ሰብሎች ማለትም ድንች ፡ በቆሎ ፡ የበልግ ጓሮ አትክልት ፡ ቦዬና ጎደሬ ሰብሎች ላይ በእቅዱ መሰረት ሙሉ በሙሉ ተሸፍኗል ያሉት ሀላፊ በዚህ 6 ሺ 824 አርሶአደሮች ተሳታፊ ሆነዋል ብለዋል ።

ለዚህም 3ሺህ 800 ኩንታል የአፈር ማዳበሪ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን 55ሺ 468 ኩንታል ምርጥ ዘር አርሶአደሩ በዚህ በልግ ልማት መጠቀሙንም አቶ ተካ አስረድተዋል ።

አቶ ተካ አያይዘውም በበልግ እርሻ ልማት 883 ሺህ 575 ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ግብ መጣሉን ጠቁመው ምርቱም ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን የክትትልና ድጋፍ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።

ቅኝት ካደረግንባቸው ቀበሌዎች መካከል የቀጣነ ቀበሌ አንዱ ሲሆን በቀበሌው የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁ አንለይ በቀበሌው በተለይም የዘር ድንችና የምግብ ድንች ሰብል በበልግ ልማት 180 ሄክታር በዘር የተሸፈነ ሲሆን 624 አርሶአደሮች መሳተፋቸው ገልፀው ለዚህም አስፈላጊውን ግብዓትና ምርጥ ዘር ተጠቅመዋልም ብለዋል ።

አርሶአደር ይትባረክ ገ/ማርያም የቀጣነ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ በበልግ እርሻ ልማት የድንች ሰብልና የጓሮ አትክል በመጠቀም ከራሳቸው አልፈው ለገበያ ለማቅረብ የግብርና ባለሙያ ድጋፍና ምክር በመስማት በስፋት እየሰራን ነው ብለዋል ።

አርሶአደሩ አክለውም ምንም እንኳ የዝናብ እጥረት ቢከሰትም በማሳቸው ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ በአግባቡ በመስራታቸው የከፋ ጉዳት እንዳያመጣ እንደጠቀማቸውም ተናግረዋል ሲል መረጃው ያደረሰን የወረዳው የመንግት/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *