በስፖርቱ ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣና በዳኞች ላይ የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተት ለመሙላት ለ10 ተከታታይ ቀናት በቮሊቮልና በባህል የስፖርት አይነቶ የዳኝነት እጥረት ለመቅረፍ በወለቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።

በስፖርቱ ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣና በዳኞች ላይ የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተት ለመሙላት ለ10 ተከታታይ ቀናት በቮሊቮልና በባህል የስፖርት አይነቶ የዳኝነት እጥረት ለመቅረፍ በወለቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።

በስልጠናዉ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን እንዳሉት መምሪያዉ በሁሉም የስፖርት አይነቶች ዉጤትና ስኬት እንዲመዘገብ እንዲሁም በዳኞች ላይ ያለዉን ዉስንነትና የክህሎት ክፍተት በስልጠና ለመሙላት አበክሮ ይሰራል ብለዋል።

በዞኑ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ያለዉን የዳኞች እጥረት በተገቢዉ መቅረፍ እንደሚገባና ይህንኑም ችግር ለመቅረፍ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

ለአንድ ሀገር ስፖርት እድገት በሁሉም የስፖርት አይነቶች የዳኞች ቁጥር ከፍ ማድረግና እነዚህም በእዉቀትና ህጉ በሚያዘዉ መሰረት ዉጤታማ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸዉም አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደም ሽኩር እንዳሉት በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚስተዋለዉን የዳኝነት እጥረት ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

በዚህም ባለፉት 10 ተከታታይ ቀናት በቮሊቮልና በባህል ስፖርቶች በዞኑ ባሉት ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በዳኝነት ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና መምሪያዉ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ለሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት መስጠት ችሏል ብለዋል።

ሰልጣኞች የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸዉ አሰልጣኞች ያለባቸዉን የእዉቀት ክፍተት መሙላት የቻሉና በቮሊቮልና በባህል የስፖርት አይነቶች የሚታየዉን የዳኝነት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ስልጠናም እንደነበረም አብራርተዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሀንስ ገብሩ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው በጤና፣ በግብርና እና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማህበረሰቡን ለመደገፍ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው በስፖርቱ ዘርፍም የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የመረብ ኳስ የ1ኛ ደረጃ እና የ2ኛ ደረጃ የባህል ስፖርት ዳኝነት ሰልጣኞችም ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም በዞኑ እየታየ ያለውን ውጤት ከፍ አድርጎ ለማስቀጠል በትጋት እንዲሰሩ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።

በዩኒቨርሲቲው የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እና የስልጠናው አስተባባሪ ዶክተር አብዱላዚዝ ሙሰማ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከጉራጌ ዞን ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር በስፖርቱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት እና በመቅረፍ ረገድ እያደረገ ያለው ድጋፍ እጅግ የሚበረታታ ነው በማለት ምስጋና ችረዋል።ሀ

በመጨረሻ ለተከታታይ አስር ቀናት በቮሊቮልና በባህል ስፖርቶች የአሰልጣኞች ስልጠና የተከታተሉ ሰልጣኞች የእዉቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *