”በስልጣኔ ቀደምት የሆኑ ሀገራት ስለሴቶች መብት መከራከር ባልጀመሩበት ወቅት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከጥንት ጀምሮ እናት ትከበርና ትመሰገን ነበር”

”በስልጣኔ ቀደምት የሆኑ ሀገራት ስለሴቶች መብት መከራከር ባልጀመሩበት ወቅት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከጥንት ጀምሮ እናት ትከበርና ትመሰገን ነበር”

የጉራጌ ብሔር ለመላው አለም ትምህርት ሊሆኑ የሚችሉ ባህልና እሴት እንዳለው የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ።

ይህ የተገለፀው የ”አንትሮሸት” የእናቶች በአል በጉራጌ ዞን እምድብር ከተማ በዛሬው እለት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት በተከበረበት እለት ነው።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንደገለፁት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ካሉት በርካታ ባህላዊ ክዋኔዎች መካከል በወርሃ ጥር የሚከበረው “አንትሮሸት” የእናቶች በዓል አንዱ ነው።

ይህም በስልጣኔ ቀደምት የሆኑ ሀገራት ስለሴቶች መብት መከራከር ባልጀመሩበት ወቅት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከጥንት ጀምሮ እናት ትከበርና ትመሰገን እንደነበር ማሳያ ነው ብለዋል ።

አንትሮሸት” የእናቶች በዓል አከባበር አጀማመርና ትርጉሙ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ተጠንቶ ይፋ መደረጉን ያስረዱት ወይዘሮ መሰረት ባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ በየአመቱ እንዲከበርና አለምአቀፍ እውቅና እንዲኖረው እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ በዓል በሁሉም ወረዳና ቀበሌ እስከ ጥር 20 የሚከበር ይሆናል።

በዛሬው እለትም በቸሀ ወረዳ ደረጃ የጉራጌ እናቶች፣ የባህል ሽማግሌዎች፣ የብሔረሰብ ተወካዮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተከብሯል።

ዞን አቀፍ የሆነው ”አንትሮሸት” የእናቶች በዓል ለማክበር የዞኑ ሴቶችና ህፃናት፣የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እንዲሁም የቸሀ ወረዳ አስተዳደር በጋራ እየተዘጋጁ እንደሆነ ወይዘሮ መሠረት አክለው ገልፀዋል።

የእምድብር ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት ወርቅነህ እንደገለፁት አንትሮሽት ለረጅም አመታት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ እናቶች የትውልድ ቀጣይነት እንዳይቋረጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ድካማቸውን በማሰባሰብ ከስራ አርፈው በልጆቻቸው እንክብካቤ የሚደረግላቸው እለት ነው ።

በበዓሉ እለትም እናቶች ለሀገር ክብርና ለትውልድ ሽግግር ካበረከቱት ባሻገር ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አስተዋጽኦ እንዲሁም ለሴት ልጅ መብትና ነፃነት ክብር የሚያጎናጽፍ ባህላዊና ታሪካዊ በዓል በመሆኑ ለአለም ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት አስረድተዋል።

ወይዘሮ መዳኒት ስዩም እና የማነሽ ሀይለማርያም የበአሉ ተሳታፊ እናቶች ሲሆኑ ሁለቱም በሰጡት አስተያየት አንትሮሽት ለጉራጌ እናቶች ክብር፣ ፍቅርና እድገት መሰረት የጣለ ባህላዊ በዓል ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የአንትሮሽት በዓል ከዘመናት በፊት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ሲከወን የኖረና በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ መድረሱን የጠቆሙት ተሳታፊዎቹ የአሁኑ ትውልድ ተረክቦ ባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ ማስቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *