በሴቶች ላይ የሚከሰተው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ለመከላከል እየሰራ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።


በዘመቻ በሚሰጠው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት ልጃገረዶች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው ተገልጿል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን እንደገለፁት የማህፀን በር ካንሰር የተለመደና በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የካንሰር ዓይነት ሲሆን ምልክት ሳያሳይ የሴቶችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ነው፡፡

በሀገሪቱ ብሎም በዞኑ የማህጸን በር ካንሰር በሴቶች ላይ የሚያሳድረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመከላከል የክትባት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል ኃላፊው።

እንደ አቶ ሸምሱ ገለፃ የማህጸን በር ከጫፍ ካንሰር በየአመቱ እድሜያቸው 14 ዓመት የሆነ ልጃገረዶች የክትባት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አገልግሎቱ በዚህ ዙርም ከጥር 02-06/2014 በትምህርት የቤቶችና በጤና ተቋማት ይሰጣል ብለዋል።

በመሆኑም መምህራን፣ የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ልጃገረዶች የክትባት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አክለውም በኃላፊው ባለፉት ስድስት ወራት ምርመራ ካደረጉ 3 መቶ ልጃገረዶች 6ቱ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።

ይህንን አሳሳቢ የሆነው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ለመከላከል ልጃገረዶች ክትባቱን በመከተብ ወደ ፊት ሊገጥማቸው የሚችለው የካንሰር በሽታ አስቀድመው ለመከላከል ያስችላቸዋል ብለዋል ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *