በማዕድን ዘርፍ አነስተኛ ባለሀብቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ በማድረግ በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ።

መጋቢ

የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ አየለ ፈቀደ እንዳሉት ባለፉት ስድስት ወራት መምሪያዉ የማህበረሰቡን የንጹሁ መጠጥ ዉሃ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱም ተናግረዋል።

በከተማና በገጠር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሆነም ጠቁመዉ በመስኖ ዘርፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሆነም አመላክተዉ በማዕድን ዘርፍ አነስተኛ ባለሀብቶች የሚያሳትፍና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

ከወረዳዎችና ከሚመለከታቸዉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት በተቋሙ የተያዙ ግቦች ማሳካት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ቦጋለ ወልዴ እንዳሉት በተቋሙ የተያዙ ግቦች ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላቶች በመተጋገዝና በቅንጅትበመስራት በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣት እንደሚገባም አመላክተዋል።

አብዛኛ አካባቢዎች በግንባታ ላይ የነበሩ የመስኖ ፕሮጀክቶች እንዳሉም አንስተዉ እነዚህም እንዲጠናቀቁም ክልሉና ፌዴራል አካባቢዎች ማገዝ እንዳለባቸዉም አብራርተዋል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የጉራጌ ዞን ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ጥገና ተቋም አሰተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪና የልማት ዕቅድ ተወካይ አቶ አብድልፈታ ያሲን እንዳሉት መምሪያው የማህበረሰቡን የንጹሁ መጠጥ ዉሃ ችግር ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በ2016 ዓመተ ምህረት የዞኑ ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚያስችል እቅድ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

በተለያዩ የዉሃ ግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ ኮንትራክተሮች ላይ የአቅም ዉስንነት የሚስተዋልባቸዉ እንደሆነም አመላክተዉ የጥገናና የጥናት ዲዛይን መሳሪያዎች እጥረትና መሰል ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

በየአካባቢዉ ያለዉን የማእድን ሀብት በተገቢዉ በመጠቀምና በዘርፉ ለዜገች የስራ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

በምክክር መድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለ ድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት ዉሃና ህይወት እንደማይነጣጠሉና የማህበረሰቡ የዉሃ ፍላጎት በጣም ከፍተኛ እንደሆነም ተናግረዉ ካለዉ ፍላጎት አንጻር መሰራት ያለባቸዉ ሰፊ ስራዎች መኖራቸዉም ጠቁመዋልኀ።

ህብረተሰቡ መጠቀም የሚችልባቸዉና በቀላሉ መጠን የሚችሉ የምንጭ ፣ የጥልቅ ጉድጓድ የዉሃ አማራጮች ህብረተሰቡ መጠቅም በሚችል መልኩ መጠገን ይገባል ብለዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *