በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ክላስተር መሰረታዊ ድርጅት አባላት ኮንፈረንስ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

“ከእዳ ወደ ምንዳ በአባላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ኮንፈረንስ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ክላስተር መሰረታዊ ድርጅት ኮንፈረንስ ውይይት ያስጀመሩት በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ እንዳሉት ፓርቲው ባለፉት ሁለት አመት ተኩል በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በሰላም ስኬታማ የሆኑ ድሎችን ማስመዝገብ ተችሏል።

በሌላ መልኩ እንደ ሀገር ትላልቅ ፈተናዎችና ችግሮችን የተጋረጡበትና ፈተናዎችንም ያለፍንበት ነው ብለዋል።

የኮንፈረንሱ አላማ ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል ፓርቲው ያከናወናቸው ተግባራቶችንና ጥሩ ልምዶችን ለማስፋትና የነበሩ ጉድለቶችን በማረም ለቀጣይ ጉዞ ለማስተካከል ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአንድን ፓርቲ ጥንካሬው የሚለካው ጠንካራ አባላት ሲኖረው መሆኑን ያነሱት ዶክተር መሀመድ ኮንፈረንሱ አዳዲስ አባላት ለማፍራትና ያሉትን አባላት ለማጠናከር ፋይዳው ትልቅ እንደሆነ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ ተናግረዋል

የክላስተሩ መሰረታዊ ድርጅት ሰብሳቢና የክልሉ የውሃ መስኖና ኤነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ የመሰረታዊ ድርጅት አባላት በማጠናከር የፓርቲው የመፈጸም አቅም ይበልጥ ማጎልበት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በኮንፈረንሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ፣ የክላስተሩ መሰረታዊ ድርጅት ሰብሳቢና የክልሉ የውሃ መስኖና ኤነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ፣ የክልሉ የወልቂጤ ክላስተር ከፍተኛ አመራሮችና የመሰረታዊ ድርጅት አባላቶች ተገኝተዋል።

ዝርዝር መረጃዉን ተከታትለን እናደርሶታለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *