በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ጉራጌ ዞን የወከለው ቸሀ የጆካ እግርኳስ ቡድን ወደ እምድብር ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን እንደገለጹት ጉራጌ ዞን በዘንድሮ የመጀመሪያው የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድር በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ የነበረ ሲሆን በእግር ኳስ ብቻ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ የነበረ ቢሆንም በዚህ ሻምፒዮን ግን የእግር ኳስ ዋንጫውን መመለስ ተችሏል ብለዋል።

በክለቦች ሻምፒዮና ይህ ውጤት ለጉራጌ ዞን በታሪክ የመጀመሪያ ጊዜ ነው ያሉት ኃላፊው ቸሀ የጆካ እግርኳስ ቡድን መላው ጉራጌ ዞንን ወክሎ የተጫወተ ሲሆን ውጤቱም ለመላው ጉራጌ በመሆኑ ቡድኑ ይበልጥ በማጠናከር በቀጣይ የተሻለ ደረጃ ላይ በማድረስ ወደ ፕሪሜርሊግ እንዲያድግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

አቶ ፈይሰል አክለውም በዞኑ የተገኙ የስፖርት ውጤቶች በቀጣይ ተተኪ ስፖርተኞች በይቻላል፣በአሸናፊነት መንፈስ እንዲሰሩ እንደሚያደርጋቸው ጠቁመው ለዚህ ውጤት መሳካት በበጀትና በተለያዩ ጉዳዮች ድጋፍ ለአደረጉና ለሚያደርጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የዞኑ መንግስት፣ ባለሀብቱ፣ማህበረሰቡና ደጋፊው ከተባበረ ከዚህ የበለጡ የስፖርት ቡድንች አፍርቶ ማስተዳደር እንደሚቻል አመላክተዋል።

የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ሽምንሳ ስፖርት ለኢኮኖሚ፣ለእርስ በርስ ግንኙነት፣ለሰላምና ለአንድነት በበአጠቃላይ ለሀገር አድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

በተለይ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀበሌ እና በትምህርት ቤቶች ውድድር በማድረግ ተጫዋቾች የተመለመሉ ሲሆን ህብረተሰቡ፣የመንግስት ሰራተኛው እና የሚመለከታቸው አካላት በገንዘብና በሌሎችም እየደገፉ እንደሆነ ተናግረዋል።

አቶ ጥላሁን አክለውም እነዚህ ጠንካራ ተጫዋቾችን በማጠናከር ፣ቡድኑ ህዝባዊ መሰረት በማሰያዝ፣ከባለሀብቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ቸሀ የጆካ ቡድን የበለጠ በማሳደግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የጉራጌ ማህበረሰብ ስም የሚያስጠራ ቡድን እንዲሆን አበክረን እንሰራለን ነው ያሉት።

የቸሀ ወረዳ ወጣትችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈታ ተጫዋቾ፣ህዝቡ፣መንግስት እና ደጋፊው በሰራው ስራ ይህ ውጤት ማምጣት የተቻለ ሲሆን የሀላባ ማህበረሰብ እና ለቡድኑ ድጋፍ ላደረጉ አካላት አመስግነዋል።

አያይዘውም ኮከብ ተጫዋች፣ኮከብ ግብ አግቢ እና ኮከብ አሰልጣኝ የዚሁ ቡድን ተጫዋቾችና አሰልጣኝ ሲሆኑ ቡድኑ ከተደገፈ ገና የበለጠ ውጤት ማምጣት የሚችል መሆኑን አቶ ደሳለኝ አስገንዝበዋል።

የቸሀ ጆካ እግር ኮስ ቡድን አሰልጣኝ አቶ ቢላል አብራር ጫዋታው ከፍተኛ መሰዋትነት የተከፈለበት ሲሆን በተለይ የተጫዋቾች፣የአሰልጣኝ እንዲሁም የደጋፊው አንድ መሆን ለውጤቱ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

የቸሀ ጆካ እግር ኮስ ቡድን በአንድ አመት ከ3 ወር ውስጥ ብቻ ጉራጌ ዞንን ወክሎ የተጫወተው ጨምሮ በተለያየ ጊዜ ለፍጻሜ ደርሶ 4 ዋንጫዎችን ማምጣት መቻሉ ገልጸው በቀጣይ ድሬዳዋ ላይ ለሚዘጋጀው ሀገር አቀፍ የክለቦች ውድድር አሸናፊ እንዲሆን የበለጠ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የሻምፒዮኑ ኮከብ ተጫዋች እና የቡድኑ አምበል ወጣት ግሩም እና ኮከብ ግብ አግቢ ወጣት ሀይደር ሽኩር በጋራ በሰጡት ሀሳብ በየጊዜው በሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮች መላው የቸሀ እና የጉራጌ ማህበረሰብ ስም ለማስጠራት በቁርጠኝነት እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።

በቡድኑ በርካታ አቅም ያላቸው ተጫዋቾች እንዳሉ የገለጹ ሲሆን እነዚህ ተጫዋቾች የበለጠ በመደገፍ፣ ብቃታቸው በማሳደ እና በመመልመል በክለብ እንዲሳተፉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለው ቀጣይ በድሬዳዋ ከተማ ላይ በሚደረገው ጨዋታ ውጤቱ ለመድገም እንሰራለን ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *