በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ234 ሚሊየን በላይ ብር ለመማሪያ መጽሀፍት ህትመት ከህረተሰቡ ማሰባሰብ መቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ፣

በክልሉ በተያዘው የትምህርት ዘመን ከ50 ሺ በላይ የመማሪያ መጽሀፍት ታትመው ለተማሪዎች ተደራሽ መደረጋቸዉም ተመላክቷል፤

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የትምህርት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንደገለጹት በክልሉ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ለመጽሀፍት ህትመት ሀብት የማሰባሰብ ዘመቻ እየተካሔደ ነው ።

በክልሉ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ለተማሪዎች በቂ መጽሀፍት ማቅረብ አለመቻሉን የተናገሩት አቶ አስከብር በተያዘው ዓመት ችግሩን ለመቅረፍ ” አንድ መጽሀፍ ለልጄ ” በሚል መሪ ሀሳብ የመጽሀፍት ህትመት ሀብት የማሰባሰብ ዘመቻ እየተካሔደ ነው ብለዋል።

እስካሁን ባለው አፈጻጸም በክልሉ ከ234 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ተሰብስቧል ያሉት ኃላፊው ከ50 ሺ በላይ መጽሀፍት ታትመው ለተማሪዎች ተደራሽ መደረጉንም አቶ አስከብር አብራርተዋል።

የስርዓተ ትምህርት ለውጥ ማድረግ ተከትሎ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የክልሉ ትምህርት ቢሮ መጽሀፍት በማሳተም ሙሉ ብለዋል።

የትምህርት ጥራት ተግዳሮት የሆኑ ችግሮችን ለመለየት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ነው ያሉት አቶ አስከብር ህብረተሰቡን በማሳተፍ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር እንደገለጹት በዞኑ እያጋጠመ ያለውን የትምህርት ጥራት ችግር ለመቅረፍ መላውን ህብረተሰብ ያሳተፈ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በትምህርት ጥራት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት የመማሪያ መጽሀፍት ህትመት ስራ ላይ ትኩረት መደረጉን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው ለዚህም ይረዳ ዘንድ በተያዘው የትምህርት ዘመን 71 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን ባለው ሂደት 47 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል።

በዞኑ የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ለመጽሀፍት ህትመት ሀብት በማሰባሰብ ከ13ሺ በላይ መጽሀፍት ለስርጭት ማብቃት ስለመቻሉም ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል።

በወራቤ ከተማ ያነጋገርናቸው ወላጆች እንደገለጹት በአካባቢያቸው ያጋጠመውን የመማሪያ መጽሀፍት ህትመት ችግር ለመቅረፍ ህብረተሰቡን በማስተባበር ያከናወኑት ሀብት የማሰባሰብ ስራ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የትምህርት ጥራትን እና የተማሪዎችን ስነ ምግባር ለማሻሻል እያከናወነ ያለውን ስራ ከግብ ለማድረስ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *